በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በወልቃይት የወከባ ስሞታው እንደቀጠለ ነው


ወከባ የሚደርስባቸው አካባቢያቸው “ወደ ትግራይ መካለሉ አግባብ አይደለም፣ የእኛ ክልል አማራ ነው” የሚል ጥያቄ በማንሣታቸውና ጥያቄአቸውንም በፊርማ አስደግፈው ወደ አዲስ አበባ፣ ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት አቤቱታ በመላካቸው እንደሆነ ነዋሪዎቹ እየተናገሩ ነው።

ወደ ዝግጅት ክፍላችን ከወልቃይት የሚደውሉ የአካባቢው ነዋሪዎች የተለያየ ገፅታ ያላቸው ጥቃትና ወከባ እየተፈፀመብን ነው እያሉ ነው።

እንዲህ ዓይነቱ ወከባ የሚደርስባቸው አካባቢያቸው “ወደ ትግራይ መካለሉ አግባብ አይደለም፣ የእኛ ክልል አማራ ነው” የሚል ጥያቄ በማንሣታቸውና ጥያቄአቸውንም በፊርማ አስደግፈው ወደ አዲስ አበባ፣ ወደ ፌደሬሽን ምክር ቤት አቤቱታ በመላካቸው እንደሆነ ነዋሪዎቹ እየተናገሩ ነው።

ወደ ፖሊስ ጣቢያ እየተጠሩ እንዲፈርሙ መደረጉ አሁንም እንደቀጠለ መሆኑን፤ ከየት እንደመጡ የማያውቋቸው ሰዎች አሁንም ሰዉን እያስፈራሩ መሆናቸውን አመልክተዋል።

በተጨማሪም “የኪነት ቡድን ወደ አካባቢው እየላኩ በዘፈን ያስሰድቡናል፤ ያስፈራሩናል” ብለዋል።

ከአካባቢውና ከክልሉ ባለሥልጣናት ስለሁኔታው ተጨማሪ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሣካም።

ይሁን እንጂ የትግራይ ክልል ፕሬዚዳንት የመሩት ከአራት ወረዳዎች የተወከሉ ስድስት መቶ ሰዎች የተሣተፉበት ጉባዔ ሰሞኑን በሁመራ አካባቢ የተካሄደ ሲሆን የክልሉ የፀጥታና የአስተዳደር ኃላፊ አቶ ሐድስ ዘነበ ሲናገሩ “.. የሌለ ድርሰት - የማንነት ጥያቄ እያስነሱ እርስ በራሱ እንዲጫረስ፣ ከልማት ጎዳና ለማስወጣት እየሠሩ ይገኛሉ።” ብለዋል።

ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

በወልቃይት የወከባ ስሞታው እንደቀጠለ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:42 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG