በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አዲሶቹ የሮለር ኮስተርስ የልብ ትርታን የሚያንሩ ተሽከርካሪዎች


ቨርችዋል ሪያሊቲ የሚባል ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ ሮለር ኮስተሮች
ቨርችዋል ሪያሊቲ የሚባል ቴክኖሎጂ የሚጠቀሙ ሮለር ኮስተሮች

በርካታ ሰዎች በተለያዩ መዝናኛ ቦታዎች በሚገኙ በፍጥነት ከፍና ዝቅ እያሉ በሚምዘገዘጉ ተሽከርካሪ መሰል የሮለር ኮስተርስ (Roller Coasters) ይዝናናሉ። ለአዲሱ ትውልድ በአዲስ ቴክኖሎጂ የተሰራው Roller Coasters በምናብ የሚያሳዩ ታምራዊ የእይታ ቴክኖሎጂዎች ተገጥሞላቸዋል። በአሁኑ ሰዓት በሰሜን አሜሪካ በሚገኘው ቲም ፓርክ (Theme Park)፣ በአውሮፓና በእስያ አዲሶቹ የቴክኖሎጂ ግኝቶች በግልጋሎት ላይ ውለዋል።

ከዚህ ቀደም የነበረው በአዲስ ሞዴል ተቀይሮ የሳምሰንግ (Samsung) የጆሮ ማጉሊያ በተጨማሪ ተገጥሞለታል፤ ከሳምሰንግ ስልክ ጋር የተያያዘ መነፅርም አለው።

ይህ አዲስ ቴክኖሎጂ አቅጣጫን የሚጠቁም ሳጥን የተገጠመለት ሲሆን የመዝናኛው ተሽከርካሪ ወዴትም ቢዟዟር ቦታውን በትክክል ይጠቁማል። እንዲሁም በአይን የሚታየውን የሚገልፅ ገመድ አልባ መዳመጫ ተያይዞለታል።

አምራች ኩባንያው እንደገለፀው ሁሉም የሮለር ኮስተርስ (Roller Coasters) እንደዚህ አዲሰ ቴክኖሎጂ የፈጠራ ምናባዊ እይታ የሚሰጠውን ደስታ ላይሰጥ ይችላል።

ቨርችዋል ሪያልቲ በሚባል ቴክኖሎጂ ተጠቅመው የሚሰሩ አዲሶቹ ሮለር ኮስተርስተሮች የልብ ትርታን የሚያንሩ ተሽከርካሪዎች
ቨርችዋል ሪያልቲ በሚባል ቴክኖሎጂ ተጠቅመው የሚሰሩ አዲሶቹ ሮለር ኮስተርስተሮች የልብ ትርታን የሚያንሩ ተሽከርካሪዎች

አዳዲሶቹ ሮለር ኮስተርስ ከነሃስ ነው የተሰሩት። በቀላሉ የሚታዘዙ እንዲሁም በሰማይ ላይ በምናብ ከተፈጠረው ከተማ ውስጥ ከሌላ አለም ፍጡራን ጋር የሚያዝናና ግጥሚያ እንዲያደርጉ ይረዳሉ።

በሰሜን አሜሪካ የሚገኘው ናይን ሲክስ ፍላግስ (Nine Six flags) የመዝናኛ ቦታ በዚህ አመት አዲሱን የምናባዊ እውነት ቴክኖሎጂን ለመዝናኛነት ለተጠቃሚ ያቀርባል። ትግልንና አዲስ ነገርን ለሚወዱት ተጠቃሚዎች ከዚህ ቀደም ከነበረው በጣም የተለየም ነው።

ዘጋቢያችን ኤልሳቤጥ ሊ (Elisabeth Lee) በስፍራው ተገኝታ ከነኚህ ድንቅ ግኝቶች በአንዱ ተሳፍራ ያጠናቀረችውን ዘገባ መስታወት አራጋው ይዛ ቀርባለች። ከበታች ያለውን የድምፅ ምልክት በመጫን የድምፅ ፋይሉን ያዳምጡ።

አዲሶቹ የሮለር ኮስተርስ የልብ ትርታን የሚያንሩ ተሽከርካሪዎች!
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:01 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG