በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሙስሊም መሪዎቹን ፍርድ የአሜሪካው የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሺን አወገዘ

ዶ/ር ሮበርት ጆርጅ፤ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሺን (USCIRF) ሊቀመንበር
ዶ/ር ሮበርት ጆርጅ፤ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሺን (USCIRF) ሊቀመንበር

ኢትዮጵያ ውስጥ በታሠሩት 18 ሙስሊም መሪዎች ላይ የተላለፈውን የእሥራት ፍርድ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሺን (USCIRF) አጥብቆ አውግዟል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሺን (USCIRF)
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሺን (USCIRF)

please wait

No media source currently available

0:00 0:01:36 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ኢትዮጵያ ውስጥ በታሠሩት 18 ሙስሊም መሪዎች ላይ የተላለፈውን የእሥራት ፍርድ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሺን (USCIRF) አጥብቆ አውግዟል፡፡

ኮሚሺኑ ባወጣው መግለጫ በአወዛጋቢው የኢትዮጵያ ፀረ-ሽብር ሕግ ክሥ ተመሥርቶባቸው ጥፋተኝነት የተበየነባቸው መሪዎች እንዲለቀቁ ለረዥም ጊዜ ሲሟገት መቆየቱን አስታውቋል፡፡

የኮሚሺኑ ሊቀመንበር ዶ/ር ሮበርት ጆርጅ በሰጡት መግለጫ ሰዎቹ ለሃይማኖት ነፃነት በሰላማዊ መንገድ ሲሟገቱ የነበሩ ናቸው ብለው የፍርድ ሂደቱ የኢትዮጵያ መንግሥት የደነገገውን ፀረ-ሽብር ሕግ ለሰብዓዊ መብቶች መከበር የሚሟገቱትንና ተቃዋሚዎችን ለማፈን መጠቀሙን እንደቀጠለ የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

አራት ተከሣሾች በሃያ ሁለት ዓመት፤ ሌሎች ደግሞ ከሰባት እስከ አሥራ ስምንት ዓመት እሥራት ተፈርዶባቸዋል፡፡

ከመካከላቸው ቅሬታ ያደረባቸው ሙስሊሞች ብሶታቸውን ለኢትዮጵያ መንግሥት እንዲያሰሙላቸው የተወከሉ የመፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት፣ ጋዜጠኞችና ሌሎችም የመብቶች ተሟጋቾች ያሉባቸው መሆኑን መግለጫው አትቷል፡፡

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ይህንንና በሌሎችም የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ይካሄዳል ያለውን ያለአግባብ የመወንጀል ተግባር በይፋ እንዲያወግዝ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ የሃይማኖት ነፃነት ኮሚሺን (USCIRF) ጠይቋል፡፡

XS
SM
MD
LG