በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ United States አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገውን ጥረት አሞገሱ


የ United States አለም አቀፍ የልማት ተራድኦ ባለስልጣናት በኢትዮጵያ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ የሚደረገው ጥረት ተስፋ ሰጪ እንደሆነ ገለጹ። አስቸኳይ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ዜጎችም እርዳታውን እያገኙ ናቸው ብለዋል ባለስልጣናቱ።

በ United States አለም አቀፍ የተራዶ ድርጀት ከፍተኛ ምክትል የእርዳታ አስተባባሪ Gregory Gotlied በአዲስ አበባ ከጋዜጠኞች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ሲም አልሱ፣

“በኢትዮጵያ ረሃብ የለም እንላለን። አሁን በኢትዮጵያ ያለው ሁኔታ በሱማልያ ያለውን ሁኔታ አይመስልም። ያ ረሃብ ነው። የእነዚህ በተመጣጠነ ምግብ እጦት ከሚታይ ጉዳት በላይ ነው። እዚህ ኢትዮጵያ ግን እንዲህ አይነት ሁኔታ የለም። እና በዚያ ረገድ እዚህ ይሻላል።" ሲሉ በኢትዮጵያ ስላለው ሁኔታ አብራርተዋል።

ኤቶጵያ ውስጥ በተመጣጠነ ምግብ እጦት የተጎዱ ህጻናት ክሊኒክ ሄደው ተገቢውን ህክምና እንደሚያገኙ ከምግብ ዋስትና አኳያም ተስፋ የሚያሳድሩ አዝማምያዎች አሉ ሲሉ የአሜሪካው ባለስልጣን አስገንዝበዋል።

XS
SM
MD
LG