በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሂዩማን ራይትስ ዋች ክሥ ትኩረት እንደሚሰጥ ዩኤስኤአይዲ አስታወቀ


Visitors at Tunnel View, like Kaori Nishimura and Eriko Kuboi from Japan, pose in front of Half Dome, center facing, during the reopening of Yosemite National Park, Calif., Oct. 17, 2013.
Visitors at Tunnel View, like Kaori Nishimura and Eriko Kuboi from Japan, pose in front of Half Dome, center facing, during the reopening of Yosemite National Park, Calif., Oct. 17, 2013.

የኢትዮጵያ መንግሥት በለጋሾች የሚያገኘውን እርዳታ ተቃዋሚዎችን ለማፈን ይጠቀምበታል የሚል ክስ መስማት ከጀመሩበት ካለፈው ዓመት መጀመሪያ አንስቶ የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ የልማት ኤጀንሲ (ዩኤስኤአይዲ) ተጨማሪ ተቆጣጠሪዎችን ከኬንያ አስመጥቶ የእርዳታውን ክፍፍል ይከታተል እንደነበረ በኢትዮጵያ የተልዕኮው ኃላፊ ቶማስ ስታል ገልፀዋል፡፡

ማእከሉ ዩናይትድ ስቴትስ የሆነው የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ድርጅት ሂዩማን ራይትስ ዋች ባለፈው ማክሰኞ የኢትዮጵያ መንግሥት ከለጋሽ ሃገሮች የሚሰጠውን እርዳታ ለፖለቲካ አፈና ይጠቀምበታል፤ ለጋሽ ሃገሮች ደግሞ አይቶ እንዳላየ መሆኑን መርጠዋል፤ የሚል ዘገባ ማውጣቱ ይታወሣል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ዘገባውን "ኢትዮጵያ ላይ የቀጠለው የበቀል እርምጃ ጥቃት" ሲል ገልጾ አስተባብሏል፡፡ ከዓለምአቀፍ ማኅበረሰብ ጋር ያለው ግንኙነትም በግልፅነት ላይ የተመረኮዘ ነው ብሏል።

ለኢትዮጵያ ከፍተኛ እርዳታ ከሚሰጡ ሃገሮች አንዷ ዩናይትድ ስቴትስ መሆኗ ይታወቃል፡፡ በሰብዓዊ መብቶች ድርጅቱ ዘገባ ላይ ትዝታ በላቸው በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ ዳይሬክተርን አነጋግራለች።

ሂዩማን ራይትስ ዋች በሪፖርቱ "ኢትዮጵያ በዓለም ከፍተኛ እርዳታ ከለጋሾች ከሚቀበሉ አገሮች አንዷ ናት፤ በያመቱም ወደ 3 ቢሊዮን ዶላር በእርዳታ ታገኛለች" ብሏል። ባለፈው ወር የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት አዲስ ተጨማሪ እርዳታ ለኢትዮጵያ እንደሚሰጥ ማሳወቁና በአጠቃላይ አሜሪካ ለኢትዮጵያ የምትሰጠውን እርዳታ ጠቅሶ በዓመት 983 ሚሊዮን ዶላር መድረሱን አመልክቷል።

በተለይም ከብሄራዊ ምርጫው ቀደም ብሎ የኢትዮጵያ መንግሥት ከለጋሾች የተሰጠውን እርዳታ "ለተቃዋሚዎች መጨቆኛ ተጠቅሞበታል" ብሏል የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቱ። በኢትዮጵያ የዩናይትድ ስቶትስ ዓለም አቀፍ የልማት ተራድዖ ድርጅት (ዩኤስኤአይዲ) ዳይሬክተር ቶማስ ስታል የድርጅቱን ዘገባ "በጣም ጠቃሚ ነዉ፤ የምንሰጠው እርዳታ በአግባብ ሥራ ላይ እንዳልዋለ የሚጠቁም ማንኛውንም ክስ የምናየው አክብደን ነው" ብለዋል።

ሚስተር ስታል ይቀጥሉና "ከአንድ ዓመት በፊት ክሶቹን መስማት ስንጀምር፤ (ባለፈው ዓመት ጥቅምት፣ ኅዳርና ታኅሣስ ማለት ነው) ናይሮቢ ከሚገኘው የአካባቢው ቢሯችን ተጨማሪ ተቆጣጣሪዎችን አስገብተን የእኛን የምግብ እርዳታ ክፍፍል ሁኔታ እንዲታዘቡ አሠማርተናል፡፡ የእኛን ሥራዎች ከሚያስፈፅሙ ኮንትራክተሮች፣ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶችም ጋር ተገናኝተን እኛ የምናደርሰው ምግብም ሆነ ሌላ ማንኛውም ድጋፍ የቅርብ ክትትል ሊደረግባቸው እንደሚገባ፣ የቅርብ ተጠያቂነት እንዳለባቸውና ማንኛውንም ዓይነት አድልዎና ማግለል ለመሸከም አንዳችም ትዕግሥት የሌለውን ፖሊሲ (ዜሮ ቶለራንስ ፖሊሲ)እንደምንከተል አስታውሰናቸዋል፡፡ ሂዩማን ራይትስ ዋች እያከናወነ ላለው ተግባር አድናቆት አለን፡፡ እኔ እራሴ አግኝቻቸዋለሁ፡፡ በቀላል የምናየው ክስ አይደለም፡፡ እናም እኛ ያንን መረጃ የቁጥጥርና የተጠያቂነት አሠራሮቻችንን ለማሻሻል እንጠቀምበታለን፡፡" ብለዋል፡፡

የሰብዓዊ መብቶች ዘገባዎች መንግሥት ከለጋሾች የሚሰጠውን እርዳታ 'በፖለቲካ መሣሪያነት ይጠቀምበታል' እያሉ የኢትዮጵያን መንግሥት ሲከስሱ የሂዩማን ራይትስ ዋች የመጀመሪያው አይደለም፤ እንደ አውሮፓ አቆጣጠር በ2008 የወጣው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ዘገባ የተቃዋሚ ፓርቲ አባላት ፓርቲያቸውን አውግዘው ኢህአዴግን ከመረጡ ማዳበሪያ፣ የእርሻ አገልግሎቶች፣ በደሞዝተኝነት ተቀጥሮ ለመሥራትና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች እንደሚያገኙ፣ በኢሕአዴግ ባለሥልጣናት እንደሚነገራቸው ይጠቅሳል። "ከዚህ አንፃር አሁን በሰብዓዊ መብቶች ድርጅቱ የተነሣውን ክስ ዩናይትስ ስቴትስ የመመርመር ዕቅድ አላት ወይ?" ተብለው የተጠየቁት ቶማስ ስታል ሲመልሱ

ኢትዮጵያ ግዙፍ ሃገር መሆኗንና ከሰማንያ ሚሊየን በላይ ሕዝብ ያላት ሃገር በመሆኗ እያንዳንዱን የተናጠል ጉዳይ መፈተሽ እንደማይቻል ጠቁመው "ዋናና አስፈላጊ ነው ብለን የምናስበው እኛ የምናደርሰው ማንኛውም ድጋፍ በአግባቡ ጥቅም ላይ መዋሉን፣ አግባብነት የለለው ቦታ ላይ አለመዋሉን ማረጋገጥ የሚችሉ ጥሩ እና ጠንካራ አሠራሮች እንዲኖሩ ማድረግ ነው፡፡ የጠበቁ እንዲሆኑም ለማሻሻልም በመሥራት ላይ ነው የምናተኩረው፡፡" ብለዋል፡፡ "በርግጥ - ይላሉ የዩኤስኤአይዲው የኢትዮጵያ ተልዕኮ ኃላፊ በመቀጠል - ይህ ዘወትር የምንሠራበት አካሄድ ነው፤ ይሁን እንጂ ሂዩማን ራይትስ ዋች እንዳነሣቸው ዓይነት ክሦች በመጡልን ቁጥር በአሠራሮቻችን ውስጥ ጤነኞቹ የትኞቹ ናቸው፣ ችግር ያለባቸው አሉ ወይ፣ ብለን ለመፈተሽና ለማሻሻልስ ምን ማድረግ አለብን ብለን እንድንመለስባቸው ዕድል ይሰጡናል፡፡"

ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ከምታገኘው አጠቃላይ እርዳታ፣ ሲሦው በአሜሪካ የሚለገስ ነው። እርዳታው ሥራ ላይ የሚውልበትን ሁኔታም የተራድዖው ልዑክ ዳይረክተር ስታል ሲያስረዱ ኢትዮጵያ በአፍሪካ በሕዝብ ብዛት ሁለተኛ ሃገር መሆኗን አስታውሰው የትምህርት፣ የጤና፣ የግብርና፣ የንግድ፣ የአስተዳደርና የአቅም ግንባታን የመሣሰሉ ፍላጎቶች እንዳሏትና ሃገራቸውም በእነዚህ በሁሉም ውስጥ ተሣትፎ እንዳላት አመልክተዋል፡፡"በተጨማሪም ሰብዓዊ ድጋፍ እንሰጣለን" ብለዋል፡፡

ዩናይትድ ስቴትስ በኢትዮጵያ ለዴሞክራሲና መልካም አስተዳዳር የምትሰጠው የገንዘብ እርዳታ በግምገማ ላይ እንዳለ ዘገባዎች እንደሚጠቁሙ አንስተን ይህ ገንዘብ መቼ እንደሚለቀቅ ዳይሬክተሩን ጠይቀናቸዋል፡፡

"አሁን እኛ በግምገማ ላይ ነን - ብለው ጀመሩና ስታል - በፕሮግራሞቻችን ላይ ሙሉ ፍተሻ ማድረግ እንፈልጋለን፡፡ እኛ በየወቅቱ የምናከናውናቸውን ተግባራት ሊፈልጉ ይችላሉ፡፡ ፕሮግራሞችን አሉን፣ የሚሠሩትንና የማይሠሩም ካሉ፤ የሃገሪቱስ ፍላጎቶች ምንድናቸው? ማስተካከያዎችን ማድረግ የሚገባን ቦታዎች አሉ እያልን እንገመግማቸዋለን፡፡ አሁን የምንገኘው በእንደዚህ ዓይነት ሥራ ላይ ነው፡፡ በውስጣችንም፣ ከመንግሥትም ጋር እየተነጋገርን ነው፡፡ እናም በተሻለ መንገድ ለመሄድ የምንችልባቸውን ሁኔታዎች፣ ትኩረታችንን ልናጠናክር የሚገባንን ሥፍራዎች ለመወሰን እና የሲቪል ማኅበረሰቡን እና ሕዝቡንም ለማሣተፍ የምንችልባቸው አጋጣሚዎች ይኖሩ እንደሆነ ለመለየት በቀጣዮቹ ጥቂት ወራት ውስጥ ይህንኑ እያከናወንን እንቆያለን፡፡" ብለዋል፡፡

ቶማስ ስታል በኢትዮጵያ የዩኤስኤአይዲ ማለትም የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ እርዳታ ድርጅት ዳይሬክተር ናቸው። ለትብብራቸው እናመሠግናለን። በተጨማሪ ዘገባውን ያዳምጡ

XS
SM
MD
LG