በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጽንስ ማቋረጥ መብትን የሚደግፍ ውሳኔ ሰጠ


የዩናይትድ ስቴትስ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ክፍለ ሀገሮች ጽንስ ማቋረጥ ለሚፈልጉ ሴቶች አገልግሎቱን ለማግኘት አዳጋች የሚያደርግ ጥብቅ ህግጋት በመደንገግ የሴቶቹ ህገ መንግስታዊ መብት የመንፈግ ሆነ የመከልከል ስልጣን የላቸውም ሲል በትናንትናው ዕለት ውሳኔ ሰጠ።

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ጽንስ ማቋረጥ በህግ የተፈቀደ ሲሆን ሴቶች ድርጊቱን እንዳይፈጽሙ ለመከላከል የራሳቸውን የቁጥጥር ህጎች ያወጡ አንዳንድ ክፍላተ ሀገር አሉ። የትናንቱ የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለጽንስ ማቋረጥ መብት ተሟጓቾች አስደስቷዋል ።

አምስት ለሶስት በሆነ የድምጽ ብልጫ ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሰጠው ይህ ውሳኔ በሩብ ምዕተ ዓመት ውስጥ ከሰጣቸው የጽንስ ማቋረጥ መብት ብይኖች ከፍተኛው መሆኑ ተመልክቷዋል።

ጽንስ ማቋረጥን በተመለከተ የጠቅላይ ፍርድቤቱን ውሳኔ በመቃወም የወጡ
ጽንስ ማቋረጥን በተመለከተ የጠቅላይ ፍርድቤቱን ውሳኔ በመቃወም የወጡ

ፍርድ ቤቱ በዚህ ብይኑ የቴክሳስ ክፍለ ሀገር ክሊኒኮች የክፈለ ሀገርዋ ወግ አጥባቂ ፖለቲከኞች ዓላማ ክሊኒኮቻችንን ለማዘጋት ነው ሲሉ ያቀረቡትን ሙግት ተቀብለዋል። የጽንስ ማስገወድ መብት ደጋፊዎች ትናንት ዋሽንግተን ዲስ ውስጥ ተሰባስበው ደስታቸውን ገልጸዋል።

የደቡብ ምስራቅዋ ክፍለ ሀገር ቴክሳስ የጽንስ ማቋረጥ ኣገልግሎትየ የሚሰጡ ክሊኒኮች በአቅራቢያቸው ባለ ሆስፒታል ታካሚዎቻቸውን አስገብተው ለማከም የሚያስችል ውል ሊኖራቸው ይገባል። በሆስፒታል ደረጃ የሚሰራባቸው በውድ ዋጋ የሚገዙ መሳሪያዎች እንዲኖራቸው ያስገድዳል። ፍርድ ቤቱ ህገ መንግስቱን በሚጻረር መንገድ የሴቶችን መብት የሚጥስና በህክምናም ኣላስፈላጊ ነው በማለት በአብላጫ ድምጽ ውድቅ አድርጎታል።

የቴክሳስ አገረ ገዢ ዳን ፓትሪክ ውንጀላውን ኣይቀበሉም።እንደያውም የኛ ሕጎች ዓላማቸው የሴቶችን ጤና ለመጠበቅ ነው በማለት ይከራከራሉ።

ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የትናንቱን የጠቅላይ ፍርድ ቤት ውሳኔ የሴቶችን የስነ ተዋልዶ መብት ላይ የተደነቀረ ከህገ መንግስት ውጭ የሆነ እንቅፋት የሚያስወግድ ውሳኔ ነው በማለት ደስታቸውን ገልጸዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጽንስ ማቋረጥ መብትን የሚደግፍ ውሳኔ ሰጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:34 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የአሜሪካ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የጽንስ ማቋረጥ መብትን የሚደግፍ ውሳኔ ሰጠ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:21 0:00

XS
SM
MD
LG