በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በወሲባዊ ምግባር ብልሹነት ምክኒያት ለተ.መ.ድ. የምንሰጠውን ገንዘብ ልንቆርጥበት እንችላለን :- ሴኔተር ቦብ ኮርከር

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ወታደር እና የድርጅቱን ባንዴራ የሚያሳይ ፎቶ /ፋይል - አሶሽየትድ ፕረስ/
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ወታደር እና የድርጅቱን ባንዴራ የሚያሳይ ፎቶ /ፋይል - አሶሽየትድ ፕረስ/

ሪፑብሊካኑ ሴኔተር ቦብ ኮርከር የመንግሥታቱ ድርጅት ሰላም አስከባሪዎች በተለይም በመካከለኛ አፍሪካ ሪፑብሊክና በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ የተመደቡት ወታደሮቹ ፈጸሙት የተባለው ወሲባዊ ጥቃት እጅግ ያስቆጣቸው መሆኑን አመልክተዋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት በሰላም አስከባሪዎቹ ወሲባዊ ምግባር ብልሹነት ምክኒያት ለዓለሙ ድርጅት የምንሰጠውን ገንዘብ ልንቆርጥበት እንችል ይሆናል ሲሉ የዩናይትድ ስቴትስ የመወሰኛው ምክር ቤት የውጭ ግንኙነቶች ኮሚቴ ሊቀመንበር አስጠነቀቁ።

ሪፑብሊካኑ ሴኔተር ቦብ ኮርከር የመንግሥታቱ ድርጅት ሰላም አስከባሪዎች በተለይም በመካከለኛ አፍሪካ ሪፑብሊክና በኮንጎ ዲሞክራቲክ ሪፑብሊክ የተመደቡት ወታደሮቹ ፈጸሙት የተባለው ወሲባዊ ጥቃት እጅግ ያስቆጣቸው መሆኑን አመልክተዋል።

ፋይል ፎቶ - የዩናይትድ ስቴትስ የመወሰኛው ምክር ቤት የውጭ ግንኙነቶች ኮሚቴ ሊቀመንበር ሪፑብሊካኑ ሴኔተር ቦብ ኮርከር
ፋይል ፎቶ - የዩናይትድ ስቴትስ የመወሰኛው ምክር ቤት የውጭ ግንኙነቶች ኮሚቴ ሊቀመንበር ሪፑብሊካኑ ሴኔተር ቦብ ኮርከር

"የመንግሥታቱ ድርጅት በብቃት ማነስ ምክኒያት የምንሰጠውን ገንዘብ ብናስቀርበት ብርቱ ቅጣት ቢጣልበት። ወሳኝ የሆነውን ዓቅም ለመገንባት ከባድ ችግር ላይ ነው የሚወድቀው።" ብለዋል ሴኔተር ኮርከር።

ከስምንት ቢሊዮን ዶላሩ የድርጅቱ ዓመታዊ የሰላም ማስከበር እንቅስቃሴ በጀት ሩቡን የምታዋጣው ዩናይትድ ስቴትስ ስትሆን ብዛት ያላቸው ሴናተሮች እንዲህ ያለ መጠነ ሰፊ የወሲባዊ ጥቃት ውንጀላ እያለ የግብር ከፋዩን ገንዘብ መስጠታችንን መቀጠል የለብንም እያሉ ናቸው።

ፋይል ፎቶ - ቻዳውያን ሰላም አስከባሪዎች በአግውልሆክ የተባለች ከተማ ማሊ ውስጥ ጥበቃ ላይ እ.አ.አ. 2014
ፋይል ፎቶ - ቻዳውያን ሰላም አስከባሪዎች በአግውልሆክ የተባለች ከተማ ማሊ ውስጥ ጥበቃ ላይ እ.አ.አ. 2014

የመንግሥታቱ ድርጅት በወሲባዊ ጥቃቱ በተወነጀሉ ሰላም አስከባሪዎች ላይ ጠበቅ እያለ ርምጃ እየወሰደ ሲሆን ቢያንስ ሁለት ክፍለ ጦሮችን ወደሃገራቸው መልሷል። ይሁንና አዳዲስ ውንጀላዎች እየቀረቡ ናቸው።

VOA60 Africa - Three UN peacekeepers appear before tribunal for sexual abuse of civilians in CAR
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:00 0:00

XS
SM
MD
LG