በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕረዚዳንት ኦባማ በኩባው ጉብኝታቸው “የመጨረሻውን የቀዝቃዛው ጦርነት ርዝራዥ” እንደሚቀብሩ አስታወቁ


លោក​ប្រធានាធិបតី​អាមេរិក ដូណាល់​ ត្រាំ ផ្លុំ​ទៀន​នៅ​លើ​នំ​ខួប​កំណើត​របស់​លោក នៅ​ពេល​លោក​ចូលរួម​ក្នុង​ពិធី​ទទួល​ទាន​អាហារ​ពេល​ថ្ងៃ​ត្រង់​ ជាមួយ​នឹង​លោក​នាយករដ្ឋមន្ត្រី​សិង្ហបុរី Lee Hsien Loong នៅ​អគារ Istana ប្រទេស​សិង្ហបុរី។
លោក​ប្រធានាធិបតី​អាមេរិក ដូណាល់​ ត្រាំ ផ្លុំ​ទៀន​នៅ​លើ​នំ​ខួប​កំណើត​របស់​លោក នៅ​ពេល​លោក​ចូលរួម​ក្នុង​ពិធី​ទទួល​ទាន​អាហារ​ពេល​ថ្ងៃ​ត្រង់​ ជាមួយ​នឹង​លោក​នាយករដ្ឋមន្ត្រី​សិង្ហបុរី Lee Hsien Loong នៅ​អគារ Istana ប្រទេស​សិង្ហបុរី។

የዩናይትድ ስቴትስ ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ በኩባ ባደረጉት ታሪካዊ ንግግር ሁለቱ ሀገሮች ከባድ የግንኙነት ታሪክ ቢኖራቸውም ለኩባ ህዝብ “የሰላም መልእክት” እንሚደሚያቀርቡ ገልጸዋል። የትላንት ጉብኝታቸው የክብር ስነ-ስርአቶችና ተምሳሌታዊነት የሰፈነበት ነበር። ይሁናን በሁለቱም ሃገሮች መካከል ያለው ልዩነትም መንጸባረቁ አልቀረም።

ኩባን ለሁለተኛ ቀን የጎበኙት ፕረዚዳንት ኦባማ ትናንት ባደረጉት ንግግር የዩናይትድ ስቴትስና የኩባ ግንኙነት ከባድ ታሪክ እንዳለው አምነው በመቀበል ለኩባ ህዝብ የሰላም መልእክት አስተላልፈዋል።

“በሃቫናና በፍሎሪዳ መካከል ያለው ርቀት 145 ኪሎ-ሜትር ብቻ ቢሆንም እዚህ ለመድረስ ስቃይንና መለያየትን ባቀፉ የርእዮተ-አለምና የመሰንክሎች ታሪክ ምክንያት ረጅም ርቀት ለመጓዝ ተገደናል።”ብለዋል።

ኦባማ ይህን ንግግር ያደረጉት ኤል ግራን ተኣትራ ደ ሃቫና (El Gran Teatra de Havana) በተባለው ታሪካዊ የሀቫና ትያትር ቤት ነው።

ፕረዚዳንት ኦባማ አያይዘውም በዋሽንግተንና በሀቫና መንግስታት መካከል ልዩነት እንዳለ ግልጽ ነው። ልዩነቶቹም ችላ የሚባሉ አይደሉም። ይሁንና ሁለቱም ሀገሮች ግንኙነታቸውን በማሻሻል ረገድ ታሪክ ሰርተው ወደ ፊት መራመድ የማይችሉበት ምክንያት አይኖርም ብለዋል።

“እኔ እዚህ የመጣሁት በአሜሪካ ሀገሮች የመጨረሻውን የቀዝቃዛ ጦርነት ርዝራዥን ለመቅበርና ለኩባ ህዝብ የወዳጅነት እጅ ለመዘርጋት ነው።” ብለዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማና ፕረዚዳንት ራኡል ካስትሮ ትላንት ማታ ተገናኝተው ከተናጋገሩ በኋላ በጋራ ለጋዜጣኞች መግለጫ ሰጥተዋል። የፕረዚዳንት ኦባማ ጉብኝት አዲስ ምዕራፍ ቢከፍትም በሁለቱም ሀገሮች መካከል ያለው ስር የሰደደ ልዩነት ጎልቶ መታየቱ አልቀረም።

“ከዚህ በፊት ደጋግሜ እንደተናገርኩት ሁሉ ከአምስት ከባድ አስርተ-አመታተ በኋላ የሁለቱ መንግስቶቻችን ግንኙነት በአንድ ሌሊት ይቀየራል ማለት አይደለም። ፕረዚዳንት ካስትሮ እንደጠቀሱት ሁሉ ከአንዳንድ ከባድ ልዩነቶች ጋር እንቀጥላለን። ልዩነቶቹም ዲሞክራሲንና ሰብአዊ መብትን ያቀፉ ናቸው።”ብለዋል።

ፕረዚዳንት ካስትሮ በበኩላቸው ጓንታናሞ ወደ ኩባ እንዲመለስና ዩናይትስ ስቴትስ በኩባ ላይ የጣለችው ማዕቀብ እንዲነሳ ደግመው ጠይቀዋል።

“ዩናይትድ ስቴትስ ኩባ ላይ የደነገገችው እገዳ ቢነሳ የበዙ ነገሮች ሊደረጉ ይችላሉ። ፕረዚዳንት ኦባማና አስተዳደራቸው በጉዳዩ ላይ ያላቸውን አቋም እንገነዘባለን። የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት እገዳውን እንዲያነሳ በተደግጋሚ ጥሪ አቀርበዋል። መንግስታቸው ከቅርብ ጊዚያት ወዲህ የወሰዳቸው እርምጃዎች አዎንታዊ ናቸው። ሆኖም በቂ አይደሉም።”ብለዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማ በሀገሪቱ ስላለው የሰብአዊ መብት አያያዝ ጉዳይ ከፕረዚዳንት ካስትሮ ጋር እንደተነጋገሩ ገልጸዋል።

“ዩናይትድ ስቴትስ ዲሞክራሲን በመደገፍ መናገሩን እንደምትቀጥል ግልጽ አድርጌያለሁ። ይህም የኩባ ህዝብ የራሱን እድል በራሱ የመወሰን መብት እንዲኖረው የሚለውን ያቅፋል። የመናገር፣ የመሰብሰብና የእምነት ነጻነትን ስላቀፉ ሁለንተናዊ ሰብአዊ መብቶችን በመደገፍ መናገራችን ይቀጥላል።”ብለዋል።

ባለፈው አመት በዘፈቀደ የማሰሩ ጉዳይ ተባብሷል ይላሉ በደሴቲቱ ሃገር ያሉት ተቃዋሚዎች። አንድ አሜሪካዊ ጋዜጣኛ ኩባ ውስጥ አሉ ስላላቸው የፖለቲካ እስረኖች ለፕረዚዳንት ካስትሮ ጥያቄ አቅርቧል።

“የፖለቲካ እስረኞች የምትላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ሰጠኝና አሁኑኑ እለቃቸዋለሁ። በቃ ስም ዝርዝር ስጠኝ። የፖለቲካ እስረኞች ስትል ምን ማለትህ ነው? ስም ወይም ስማቸውን ስጠኝ። ወይም ደግሞ ይህ ጋዜጣዊ ጉባኤ ሲያበቃ የፖለቲካ እስረኞች የምትላቸውን ሰዎች ስም ዝርዝር ልትሰጠኝ ትችላለህ። የምታላቸው የፖለቲካ እስረኞች ካሉ ዛሪ ከመምሸቱ በፊት ይለቀቃሉ።”ብለዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማ በጉብኝታቸው ከኩባ የንግድ ሰዎች ጋር በቢራ መጥመቂያ ቦታ ላይ ተገናኝተውም ተነጋግረዋል። የኩባ ብሄራዊ ጀግና ሆዜ ማርቲ መታሰብያንም ጎብኝተዋል። ፕረዚዳንት ኦባማ በደሴቲቱ ሃገር የሰብአዊ መብት መጠበቅን እንደሚደግፉ ሲገልጹ ፕረዚዳንት ራኡል ካስትሮ በሀገራቸው የፖለቲካ እስረኞች እንደሌሉ አጥብቀው ተናግረዋል። አልበርቶ ፒሜንታ (Alberto Pimienta) እና ሜሪ አሊስ ሳሊናስ (Mary Alice Salinas) የላክዋቸውን ዘጋባዎች አጠናቅራ አዳነች ፍሰሀየ አቀርባዋለች።

ፕረዚዳንት ኦባማ በኩባው ጉብኝታቸው “የመጨረሻውን የቀዝቃዛው ጦርነት ርዝራዥ” እንደሚቀብሩ አስታወቁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:44 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG