በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ባራክ ኦባማ የሩስያው መሪ ከቱርክ ጋር ያለውን ውጥረት እንዳይባብስ ሃሳባቸውን አቀረቡ


Russian President Vladimir Putin, left, and President Barack Obama shake hands at the COP21 U.N. Conference on Climate Change in Paris, Nov. 30, 2015.
Russian President Vladimir Putin, left, and President Barack Obama shake hands at the COP21 U.N. Conference on Climate Change in Paris, Nov. 30, 2015.

ባራክ ኦባማ የሩስያው መሪ ከቱርክ ጋር ያለው ውጥረት እንዳይባብስ ሃሳባቸውን አቀረቡ።

የዩናትድ ስቴትስ (United States) ፕረዚዳንት ባራክ ኦባማ ቱርክ ባለፈው ሳምንት የሩስያን ተዋጊ አይሮፕላን መትታ መጣልዋ እንዳሳዘናቸው ለሩስያው ፕረዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ዛሬ ገልጸው የሩስያው መሪ ከቱርክ ጋር ያለውን ውጥረት እንዳይባብስ እንዲጥሩም ሃሳብ አቅርበዋል።

ሁለቱ መሪዎች የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሚያካሄደው የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ተገናኝተው ለ 30 ደቂቃዎች ያህል ተነጋግረዋል። ቱርክ አይሮፕላኑን ተኩሸ የጣልኩት ወደ አየር ግዛቴ ስለገባ ነው ትላለች። ሩስይ በበኩልዋ ከሶርያ ግዛት አልወጣም ብላለች። አንድ ሩስያዊ ፓይለትና አንደ የአይሮፕላኑ ሰራተኛ ተገድለዋል። ቭላዲሚር ፑቲን በበኩላቸው በቱርክ ላይ መዕቀብ በመጣል ምላሽ ሰጥተዋል።

ፕረዚዳንት ኦባማና ፕረዚዳንት ፑቲን በሶርያ ስለሚካሄደው ውጊያ እንደተነጋገሩና ሁለቱም መሪዎች የሚያስፈልገው ፖለቲካዊ መፍትሄ ነው በሚለው ነጥብ ላይ እንደተስማሙ ዋሽንግተንና ሞስኮ ገልጸዋል። በሶርያ የሽግግር መንግስት የሚመሰረት ከሆነ ፕረዚዳንት ዐሳድ ከስልጣን መውረድ ይኖርባቸዋል ሲሉ ፕረዚዳንት ኦባማ ለፕረዚዳንት ፑቲን ተነግረዋል። ይሁንና ሞስኮ ጸረ ዐሳድ ተቃዋሚዎችን በአየር መደብደብ ቀጥላለች።

ኦባማ አያይዘውም በምስራቅ ኡክራይን በመንግስትና በሩስያ ደጋፊ ተቃዋሚዎች መካከል የሚካሂደው ግጭት መቆም አለበት ሲሉ ለፑቲን ተናግረዋል። ቀደም ሲል በሚኒስክ የተደረገው የተኩስ ማቆም ስምምነት እንዲተገበርም ጥሪ አድርገዋል። የተኩስ ማቆሙ ስምምነት ከተሳካ በሩስያ ላይ የተጣለው ማዕቀብ ሊቃለል እንደሚችል ፕረዚዳንት ኦባማ ለፕረዚዳንት ፑቲን ገልጸዋል። የዜና ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምጽ ፋይል ያዳምጡ።

ባራክ ኦባማ የሩስያው መሪ ከቱርክ ጋር ያለው ውጥረት እንዳይባብስ ሃሳባቸውን አቀረቡ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:41 0:00

XS
SM
MD
LG