አዲስ አበባ —
ዩናይትድ ስቴትስ በድርቅ ለተጎዱ ኢትዮጵያዊያን መርጃ የሚሆን የ128 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍ ሰጥታለች።
የድርቁ አደጋ አሁንም አለመቀረፉን የገለፁት በዩናይትድ ስቴትስ የዓለምአቀፍ ልማት ኤጀንሲ - ዩ.ኤስ.ኤ.አይ.ዲ. የዴሞክራሲ፣ የግጭት፣ የሰብዓዊ ጉዳዮች ተጠባባቂ ረዳት አስተዳዳሪ ቶመስ ስታል መዘናጋት እንደማያስፈልግ ጠቁሟል።
በሌላ በኩል ደግሞ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥትና ሕዝብ ድጋፍ አስቸጋሪውን ጊዜ ለማሳለፍ ያገዘ መሆኑን የኢትዮጵያ የብሄራዊ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ኮሚሸነር ምትኩ ካሣ ገልፀዋል።
ለተጨማሪ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።