በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የትረምፕ ፖሊሲዎችና የአሜሪካ አገረ ገዥዎች


Trump Governors
Trump Governors

ነባሮቹን የዩናይትድ ስቴትስ የኢሚግሬሽን፣ የጤና ጥበቃና ሌሎችም ፖሊሲዎችን ለመለወጥ የጎሉ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በመጀመሪያው የዋይት ሃውስ ወራቸው ውስጥ ተናግረዋል፡፡

ነባሮቹን የዩናይትድ ስቴትስ የኢሚግሬሽን፣ የጤና ጥበቃና ሌሎችም ፖሊሲዎችን ለመለወጥ የጎሉ እርምጃዎችን እንደሚወስዱ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በመጀመሪያው የዋይት ሃውስ ወራቸው ውስጥ ተናግረዋል፡፡

እነዚያን ለውጦች ተግባራዊ ለማድረግ ግን ፕሬዚዳንቱ የአገረ ገዥዎቻቸው ድጋፍ ሳያስፈልጋቸው አይቀርም፡፡

የስቴቶች ገዥዎች ለዓመቱ የክረምቱ ወቅት ጉባዔያቸው ባለፉት ሦስት ተከታታይ ቀናት ዋሺንግተን ዲሲ ውስጥ ተገናኝተው ነበር፡፡

ፕሬዚዳንቱ ታዲያ ከትናንት በስተያ ዕሁድ ገዥዎቹን አግኝተው አሁን በሃገሪቱ ላይ የተደቀኑ ጉዳዮችን በአግባቡ ለመያዝ ዋይት ሃውስ ቤተመንግሥትና የተወካዮች ምክር ቤቱ ምን ማድረግ እንዳለባቸው ሃሣቦቻቸውን እንዲያካፍሏቸው ጠይቀዋል፡፡

በዚያው ስብሰባ ላይ የነበሩት ምክትል ፕሬዚዳንት ማይክ ፔንስ አገረ ገዥዎቹ በማንኛውም ጊዜ ዋይት ሃውስ ለመግባት ቀጠሮ ማስያዝ ወይም በር ማንኳኳት እንኳ እንደማይጠበቅባቸው ነግረዋቸዋል፡፡

“ለእያንዳንዳችሁ ልነግራችሁ የምፈልገው ነገር የቤተመንግሥቱ ዋና መግቢያ የሆነው የምዕራብ በር ለአሜሪካ አገረ ገዥዎች ክፍት መሆኑን ነው” ብለዋል ፔንስ፡፡

አገረ ገዥዎቹ ግዙፍም ሆነ ትንንሽ ከተሞቻቸውን በሚያሳስቧቸው ጉዳዮች ላይ ዋሺንግተን አብራቸው ለመሥራት ዝግጁ ስለመሆኗ እጆች የተዘረጉበት ግብዣ ነው፡፡

ብዙ ጊዜ በውስጡ ለማለፍ እጅግ የተወሳሰበና አስቸጋሪ ተደርጎ የሚወሰደውን የኢሚግሬሽን ጉዳይ ማተካከል ከባድ መሆኑን እንደሚገነዘቡ የሁለቱም ፓርቲዎች መሪዎች ተናግረዋል፡፡

የዩታ ገዥ ጌሪ ኸርበት “የወሰን ደኅንነት ጥበቃ ጉዳይ ድንበሩ ላይና በዙሪያው አጥሮችና ግንቦችን ማቆም ማለት አይደለም፡፡ መግቢያና መውጫው በር በአግባቡ ይሠራል ወይ? ሰዎች እንዴት መምጣትና መሄድ ይችላሉ? እንዴት መጥተው መጎብኘት ይችላሉ? መጥተው መቆየት፤ የሥራ ፍቃድ ማግኘት ይችላሉ ወይ? ነው በኔ አመለካከት ዋናው ጉዳይ” ብለዋል፡፡

የብሄራዊው የአገረ ገዥዎች ማኅበር ሊቀመንበር የሆኑት የቨርጂንያው ገዥ ቴሪ ማክኦለፍ ከቪኦኤ ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስ የሃገርን ደኅንነትና የሰዎችን ነፃነቶች የመጠበቅ ሥራዎች አብረው መያዝ እንዳለባቸው አሳስበዋል፡፡

“ሁላችንም የየማኅበረሰቦቻችንን ደኅንነት መጠበቅ እንደፈልጋለን፡፡ ይሁን እንጂ ሕጋዊ አግባብና ሲቪል ነፃነቶችን መርገጥ አንችልም፡፡ የሚያደርገው ቢኖር ሰዎች እንዲደበቁ መግፋት ነው፡፡ ለጤናቸው አገልግሎቶችን እንዳይጠይቁ ወይም እንዳይታከሙ፣ ከሕግ አስከባሪ አካላት ጋር እንዳይተባበሩ፤ ነዋይ፣ ጉልበት፣ ጊዜም ሆነ ዕውቀታቸውን ሥራ ላይ እንዳያውሉ ነው የምንገፋቸው፡፡ ይህ ሁኔታ ቨርጂንያ ውስጥ ምጣኔ ኃብታችንን ይጎዳል ብዬ እሠጋለሁ” ብለዋል ማክኦለፍ፡፡

በፈጣሪው ስም “ኦባማኬር” የሚል ቅጥያ በተሰጠው ለአቅም ተመጣጣኝ የሆነ የጤና ጥበቃ ዋስትና ሕግ ላይ ይወሰዳሉ የተባሉት ለውጦች እንዳሚያሳስባቸው የተናገሩ ገዥዎች በአንዳንድ ግዛቶች ውስጥ ለውጦቹ የጤና ጥበቃ ዋጋን ያንራሉ የሚል ሥጋት እንዳላቸው አመልክተዋል፡፡ የአርካንሳ ገዥ አሣ ኸትቺንሰን አንዱ “እንደ ገዥዎች የእኛ ፍላጎት ታካሚን ማዕከል ያደረገ ለአቅም ተመጣጣኝ የሆነና ሁሉም ሰው ሊያገኘው የሚችል የጤና ጥበቃ አገልግሎት መኖሩን ማረጋገጥ ነው” ብለዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ትረምፕ ከትናንት በስተያ ለገዥዎቹ ንግግር ባደረጉበት ወቅት ከምረጡኝ ዘመቻቸው ወቅት አንስቶ ይዘውት የመጡትን ቃል ደግመዋል፡፡ “አብዛኞቻችሁ እንደምታውቁት ኦባማኬር ግዙፍ ችግሮች አሉበት፡፡ እንሠርዘዋለን፤ በሌላ እንተካዋለን” ብለዋል፡፡

የገዥዎቹ ዓመታዊ ጉባዔም ቢሆን ወደፊት ለመራመድ የመማሪያ መድረክ ወይም መሣሪያ ሊሆን እንደሚችል የብሄራዊው የገዥዎች ማኅበር ዋና ሥራ አስፈፃሚ ስካት ፓቲሰን አመልክተዋል፡፡

“ሃምሣ ስቴቶች፤ አምስት ግዛቶችና ዲስትሪክት ኦቭ ኮሎምቢያ፡፡ ሙከራ ለማድረግ፤ ለፈጠራ፤ የሚሠራና የማይሠራውን ለይተን አውቀን መረጃ ለመለዋወጥ፤ የትኞቹ ፖሊሲዎች እኛ የምንፈልጋቸውን ውጤቶች የሚያስገኙልን ፖሊሲዎች ምን ዓይነቶቹ እንደሆኑ ለማወቅ፤ ለምሣሌ የተሻለ የጤና ጥበቃ አያያዝ ምን እንደሆነ ለመለየት ብዙ ዕድሎች አሉን” ብለዋል፡፡

ሁሉም አገረ ገዥዎች ከፕሬዚዳንቱ ጋር ትናንት ዋይት ሃውስ ውስጥ ተሰብስበው ፖሊሲዎቻቸውን ይነድፋሉ ተብሎ ሲጠበቅ ነበር፡፡

ዝርዝርሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የትረምፕ ፖሊሲዎችና የአሜሪካ አገረ ገዥዎች
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:42 0:00

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG