በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ የዕምነት ነፃነት ኮሚሽን ኢትዮጵያ የአምልኮ ነፃነትን ተነፍጋለች አለ


ቪክቶሪያ ኑላንድ - የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ
ቪክቶሪያ ኑላንድ - የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ

የአሜሪካ ባለሥልጣናት በኢትዮጵያ ላይ ተፅዕኖ እንዲያደርጉ ጠይቋል፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ለሙስሊም ኢትዮጵያዊያን የአምልኮ ነፃነት እየተነፈገ መምጣቱ በጥልቁ ያሳስበኛል ሲል መግለጫ አወጣ።


please wait

No media source currently available

0:00 0:03:40 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ



የአሜሪካ ባለሥልጣናት ኢትዮጵያ የሃይማኖት ነፃነትን እንድታከበር የአሜሪካ ባለሥልጣናት ለአዲሶቹ የአገሪቱ አመራር አባላት እንዲገልፁም ጠይቋል፡፡ አንድ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ መልስ ሰጥተዋል።
የዩናይትድ ስቴትስ ዓለምአቀፍ ሃይማኖት ነፃነት ኮሚሽን USCIRF ካለፈው የአውሮፓዊያን ሐምሌ 2004 ወዲህ “የኢትዮጵያ መንግሥት በመላ አገሪቱ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ የሚከተለውን የእሥልምና ዘርፍ በኃይል ለመቀየርና ይጥራል፥ እርምጃውን የሚቃወሙ የሃማኖቱን መሪዎችና ምሁራንም ይቀጣል” ብሏል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፈው ጥቅምት አሥራ ስምንት 29 ተቃዋሚዎችን “በአሸባሪነትና አገሪቱን ወደ እሥላማዊት አገርነት በመቀየር ሙከራ” ከስሷል።
ኮሚሽነር አዚዛ አል ሒቢሪ “ተከሳሾቹም በብዙ ሽህዎች የሚገመቱ ሰላማዊ የመንግሥት ፓሊሲ ተቃዋሚዎች አካል ናቸው” ማለታቸው ተጠቅሷል።
“አሸባሪነትን በመዋጋት ስም የሃይማኖትን ነፃነት መንፈግ የባሰ ማክረር፣ አለመረጋጋትና ብጥብጥን እንደሚያስከትል አረጋግጠናል” የሚለው የUSCIRF መግለጫ፥ የኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ዓለምአቀፍ የዕምነት ነፃነትን ሕግና መብቱን የሚፈቅደውን የራሣቸውን ሕገመንግሥት እንዲያከብሩ የዩናይትድ ስቴትስ ባለስልጣናት አዲሶቹን የአመራር እንዲገልፁ ጠይቋል። የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ቃል አቀባይ ቪክቶሪያ ኑላንድ በሰጡት መልስ “ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው የሰብዓዊ መብቶች ሁኔታ በጣም በግልፅነት ከመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር ስንነጋገር ቆይተናል፤ በአዲሱ አመራር ሥር ኢትዮጵያ የሰብአዊ መብቶች አያያዟን ወደ ዓለምአቀፍ ደረጃ ታሻሽላለች የሚል ተስፋ አለን” ብለዋል።
ዝርዝሩን ትዝታ በላቸው ካጠናቀረችው ዘገባ ያድምጡ
XS
SM
MD
LG