በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዓለም መሪዎች ከዩናይትድ ስቴትስ አዲስ ፕሬዚዳንት ጋር ለመሥራት ቃል እየገቡ ነው


የዓለም መሪዎች ማክሰኞ በተጠናቀቀው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዶናልድ ትራምፕ በተመረጡበት አስገራሚ ድል አስተያየታቸውን እየሰጡ ናቸው።

የሩስያው ፕሬዚዳንት ቪላዲሚር ፑቲን ዛሬ በሞስኮ ጉብኝት ላይ ካሉ የውጭ ሃገር እንግዶች ጋር በተገኙበት ሥነ ስርአት ላይ ሆነው ለተመራጩ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል።

አዲስ ተመረጩ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በምረጡኝ ዘመቻቸው ወቅት የሀገራቸውንና የሩስያን ግንኙነት ለማደስ እንደሚፈልጉ መናገራቸውን ያስታወሱት ፑቲን የሀገሮቻችንን ግንኙነት ለማደስ በጉጉት አጠብቃለሁ ብለዋል፡፡

የጀርመን ቻንስለር አንገላ መርከል
የጀርመን ቻንስለር አንገላ መርከል

በበርሊን ደግሞ የጀርመን ቻንስለር አንገላ መርከል የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዘመቻ በተደጋጋሚ

“ለመቀበል የሚከብዱ ፍጥጫዎች የተንፀባረቀበት ነበር” ካሉ በኋላ ከአዲሱ አስተዳደር ጋር አብረው እንደሚሰሩ ቃል ገብተዋል።

የቪኦኤው ጄፍ ከስተር ያጠናቀረችው ዘገባ ቆንጅት ታየ ታቀርባለች፡፡

የዓለም መሪዎች ከዩናይትድ ስቴትስ አዲስ ፕሬዚዳንት ጋር ለመሥራት ቃል እየገቡ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:07 0:00

XS
SM
MD
LG