በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናትድ ስቴትሱ ዲሞክራቲክ ፓርቲ በታሪክ የመጀመሪያዋን ሴት እጩው አደረገ


“እንደምን ዋላችሁ ልዑካን! አንዳች ታሪክ እውን ልናደርግ ተዘጋጅተናል?” የኦሃዮ ክፍለ ግዛቷ ዲሞክራት ማርሻ ፈጅ፤ የዲሞክራቲክ ፓርቲው ልዑካን ሂላሪ ክሊንተንን የፓርቲው እጩው ያደረጉበትን ድምጽ ለመስጠት በተሰናዱበት ያቀረቡት ሃሳብ አዘል ጥያቄያቸው።

ለታሪክ እንግዳ ያልሆነችው የፊላደልፊያ ከተማ አንድ ሌላ ታሪክ ከመዝገቧ አሰፈረች። በዩናይትድ ስቴትስ የፖለቲካ ታሪክ የመጀመሪያዋ ሴት የፓርቲያቸው ፕሬዝዳንታዊ እጩ ሆነው ቀረቡ።

በዩናይትድ ስቴትሷ የሰሜንና የመካከለኛው አትላንቲክ ክፍለ ግዛቷ ፔንሰልቫንያ ግዙፍ ከተማ ፊላደልፊያ በመካሄድ ላይ ባለው የዲሞክራቲክ ፓርቲ ጉባኤ ሁለተኛ ቀን ትላንት ምሽት ነው፤ ሂላሪ ክሊንተን የፓርቲያቸው እጩ ሆነው የጸደቁት።

ይሁንና የትላንቱም ምሽት እንደመጀመሪያው ቀን ሁሉ የሴናተር ክሊንተንን የፓርቲያቸው እጩ የተመራጭነት ይፋ ያደረጉት የቀድሞ ተፎካካሪያቸው በርኒ ሳንደርስ ደጋፊዎች በዝምታ ዘይቤ አፋቸውን በማሸጊያ ፕላስቲክ ሸብበው ያሳዩበትን ጨምሮ የጠነከረ ተቃውሟቸው አልተለየውም።

ባለቤታቸውን የቀድሞ ፕሬዝዳንት ክሊንተንን ጨምሮ በርካታ ተናጋሪዎች ሂላሪ ክሊንተን ቀጣይዋ ፕሬዝዳንት መሆን እንዳለባቸው ሴትየዋ እኚህ ናቸው ሲሉ የድጋፍ ምስክርነት ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ዝርዝር ዘገባውን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ።

የዩናትድ ስቴትሱ ዲሞክራቲክ ፓርቲ በታሪክ የመጀመሪያዋን ሴት እጩው አደረገ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:53 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG