በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር ወደ ሰሜን ኢራቅ ተጉዘዋል


የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር አሽ ካርተር የእስልምና መንግሥት ነኝ የሚለው ጽንፈኛ ቡድን ላይ የሚካሄደው ውጊያ ስለሚስፋፋበት የኩርዶች መሪዎችን ለማነጋገር ወደ ሰሜን ኢራቅ ተጉዘዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ የመከላከያ ሚኒስትር አሽ ካርተር የእስልምና መንግሥት ነኝ በሚለው ጽንፈኛ ቡድን ላይ የሚካሄደው ውጊያ ስለሚስፋፋበት የኩርዶች መሪዎችን ለማነጋገር ወደ ሰሜን ኢራቅ ተጉዘዋል።

ሚኒስትር ካርተር ዛሬ ኢርቢል አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ የኢራቅዋ ራስ ገዝ አስተዳደር ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ቁባድ ታላባኒ ተቀብለዋቸዋል።

በሁዋላ ደግሞ ከኩርድ ፕሬዚደንት ማሱድ ባርዛኒ እና በካባቢው ካሉ የዩናይትድ ስቴትስ ጋር ተገናኝተው ይነጋገራሉ።

የኢራቅ ኩርዶች ዩናይትድ ስቴትስ በምትመራው ጸረ የእስልምና መንግስት ዘመቻ ከሚካፈሉ ዋና ዋና የምድር ጦር ወታደሮች አንዱ እየሆኑ መጥተዋል። ጽንፈኛው ቡድን በተከታታይ ሽንፈት እየደረሰበት ይሁን እንጂ አሁንም ኢራቅና ሶሪያ ውስጥ ስፋት ያለው ግዛት እየተቆጣጠረ ነው።

የአሜርካው የመከላከያ ሚኒስትር ትናንት ረቡዕ ኣስቀድሞ ይፋ ባልተደረገ ጉብኝት ባግዳድ ገብተው ከጠቅላይ ሚኒስትር ሃይደር ኣል ኣባዲ እና ከመከላከያ ሚኒስትሩ ኻሊድ ኣል ኦባይዲ ጋር መወያየታቸውኛ ዩናይትድ ስቴትስ ጸረ አይስስ ዘመቻው እንዲፋጠን የምትፈልግ መሆኑን አስገንዝበዋቸዋል።

ዛሬ ሚስትሩ በሰጡት ቃል ጽንፈኛውን ቡድን ባፋጣኝ ለድል ለመምታት ምን ማድረግ እንደሚቻል ከዩናይትድ ስቴትስ የጦር ሓይል መሪዎች ጋር እንደሚወያዩ የአውሮፓም ሆኖ የሰላጤው ሃገሮች ሌሎችም አስተዋጽኦ እንዲያደርጉ ለመቀስቀስ ስለሚቻልበት መንገድ እንደሚመካከሩ ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG