በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኦስትሪያ ስደተኞችን በፀጋና እንደቤተሰብ ተቀበለች


የሦሪያ ስደተኞች - ሃንጋሪ
የሦሪያ ስደተኞች - ሃንጋሪ

በመቶዎች የሚቆጠሩ የሦሪያ ስደተኞች ከቡዳፔሽቱ ካሌቲ ባቡር ጣቢያ ተነስተው ድንበር እያቋረጡ ወደ ኦስትሪያ እየገቡ ነው፡፡

please wait

No media source currently available

0:00 0:06:33 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

በመቶዎች የሚቆጠሩ የሦሪያ ስደተኞች ከቡዳፔሽቱ ካሌቲ ባቡር ጣቢያ ተነስተው ድንበር እያቋረጡ ወደ ኦስትሪያ እየገቡ ነው፡፡

ስደተኞቹ እስከ ኦስትሪያ ድንበር እየተጓዙ ያሉት የሃንጋሪ መንግሥት ባቀረበላቸው አውቶቡሶች መሆኑም ታውቋል፡፡

በተራዘመውና አደጋና መከራ በበዛበት ጉዞ እጅግ የተጎሣቆሉና የተዳከሙት ስደተኞች ኦስትሪያ ሲደርሱ የሞቀና የእንኳን ደኅና መጣችሁ አቀባበል የተጠበቃቸው መሆኑ ተዘግቧል፡፡

ስደተኞቹ የምዝገባና የጥገኝነት ማመልከቻ አሠራሮችን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ጀርመንና ወደ ሌሎችም የአውሮፓ ሃገሮች እንደሚጓዙ ተገልጿል፡፡

የጀርመን መንግሥት ስምንት መቶ ሺህ ስደተኞችንና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ለመቀበል ቃል የገባ ሲሆን የፊንላንድ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁባ ሲፒላ ዜጎቻቸው ለስደተኞቹ በሮቻቸውን ክፍት እንዲያደርጉ ጠይቀዋል፡፡

ለአርአያነትም ከባለቤታቸውና ከከፍተኛ ሹማምንቶቻቸው ጋር ከተመካከሩ በኋላ ከምፔሌ ከተማ የሚገኘውን የራሣቸውን የግል መኖሪያ ቤታቸውን ለስደተኞቹ መጠጊያነት እንደሚለቅቁና ቤቱ ከመጭው የአውሮፓ አዲስ ዓመት ዕለት ጀምሮ ዝግጁ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

ዓርብ እና ቅዳሜ፤ ነኀሴ 29 እና 30 / 2007 ዓ.ም ብቻ ከአምስት አምስት መቶ በላይ ቁጥር ያላቸው ስደተኞች ኦስትሪያ የገቡ ሲሆን ከመካከላቸው ሩብ የሚሆኑት ሕፃናት መሆናቸው ታውቋል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ከበርካታ አሥርት ዓመታት ወዲህ ወደ አውሮፓ በመጉረፍ ላይ ለሚገኙ ስደተኞች ችግር የ 28ቱ የአውሮፓ ህብረት አባል ሀገሮች የጋራ ጥረት ሰብዓዊነትና ትክክለኝነትን የተከተለ እንዲሆን የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነር ጥሪ አቅርቧል።

በያዝነው የአውሮፓ 2015 ዓመት ብቻ አብዛኞቹ ከሦሪያ የሆኑ ተጨማሪ 200 ሺህ ስደተኞች ጥገኝነት ፍለጋ አደገኛውን ጉዞ ወደ አውሮፓ ሊያደርጉ እንደሚችሉም ዩኤንኤችሲአር አስጠንቅቋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG