በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ተመድ ደቡብ ሱዳንን በተመለከተ አዲስ ሪፖርት አወጣ


ፎቶ ፋይል፡- ደቡብ ሱዳን
ፎቶ ፋይል፡- ደቡብ ሱዳን

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ደጋፊ ኃይሎች ዬዪ ከተማ ውስጥ እአአ 2016 እስከ ጥር 2017 በነበረው ጊዜው ውስጥ ቢያንስ አንድ መቶ አሥራ አራት ሲቪሎችን መግደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው አዲስ ሪፖርት ገለጠ፡፡

የደቡብ ሱዳን መንግሥት ደጋፊ ኃይሎች ዬዪ ከተማ ውስጥ እአአ 2016 እስከ ጥር 2017 በነበረው ጊዜው ውስጥ ቢያንስ አንድ መቶ አሥራ አራት ሲቪሎችን መግደላቸውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ያወጣው አዲስ ሪፖርት ገለጠ፡፡ የተባበሩት መንግሥታት የደቡብ ሱዳን ተልዕኮ /UNMISS/ እና የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ቢሮ ዛሬ ባወጡት ሪፖርት ላይ የመንግሥት ወገንተኞቹ ሐይሎች በሲቪሎች ላይ መድፍ መተኮሳቸው ዒላማ አድርገው የገደሏቸው ሰዎች መኖራቸውንና ንበረቶች መዝረፋቸውንና መንደሮች ማቃጠላቸውን ዘርዝረዋል።

ሴቶችና ልጃገረዶችን፣ ከግጭት እየሸሹ የነበሩትንም ጭምር ደፍረዋል ብለዋል።

የተፈፀሙት ወንጀሎች በጦርነት ወንጀል፣ በሰብዕና ላይ በተፈፀመ ወንጀል ሊያስጠይቅ እንደሚችል ሪፖርቱ አክሎ አስገንዝቧል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG