በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በድርቅ የተጎዱ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት የሚያስፈልገው ገንዘብ ከ1.4 ቢሊዮን ወደ 1.5 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ማለቱን የተ.መ.ድ. ይፋ አደረገ

ድርቅ ካጠቃው አካባቢ በኦሮሚያ ክልል በሚገኝ ገልቻ መንደር ውስጥ በድርቁ ምክንያት የመነመነ በሬ እ.አ.አ. 2016 /ሮይተርስ/
ድርቅ ካጠቃው አካባቢ በኦሮሚያ ክልል በሚገኝ ገልቻ መንደር ውስጥ በድርቁ ምክንያት የመነመነ በሬ እ.አ.አ. 2016 /ሮይተርስ/

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ ባወጣው መግለጫ ገንዘቡ ቀደም ሲል ከተገመተው በላይ መጨመሩን አስታውቋል።

በድርቅ የተጎዱ ኢትዮጵያውያንን ለመርዳት የሚያስፈልገው ገንዘብ መጠን ቀደም ሲል ከተገመተው በላይ መጨመሩን፥ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ እርዳታ ማስተባበሪያ ቢሮ አስታውቋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅና የምግብ እጥረት ሁናቴ በቅርብ ለመከታተል ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት የተነሳ ፎቶ
የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሓፊ ባን ኪ ሙን በኢትዮጵያ የተከሰተውን ድርቅና የምግብ እጥረት ሁናቴ በቅርብ ለመከታተል ወደ ኢትዮጵያ በተጓዙበት ወቅት የተነሳ ፎቶ

በዚህም መሠረት፥ የሚያስፈልገው ገንዘብ ከአንድ ነጥብ አራት ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወደ አንድ ነጥብ አምስት ቢሊዮን ከፍ ማለቱን ይፋ አድርጓል።

እስክንድር ፍሬው የላከውን ዝርዝር ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

ተመሳሳይ ርእስ

XS
SM
MD
LG