በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ልዑካን በስደተኞች መጠለያ ጉዳይ ላይ ለመወያየት በናይሮቢ ጉብኝት አደረጉ


የሶማልያ ስደተኞች በዳዳብ የስደተኞች ካምፕ የምግብ ራሽን እየተቀበሉ እ.አ.አ. 2013/ፋይል ፎቶ/
የሶማልያ ስደተኞች በዳዳብ የስደተኞች ካምፕ የምግብ ራሽን እየተቀበሉ እ.አ.አ. 2013/ፋይል ፎቶ/

የጸጥታ ምክር ቤቱ ልዑካን በናይሮቢ ከኬንያ ፕሬዚደንት ኬኒያታ ጋር ከተነጋጋሩ በኋላ የመንግስታቱ ድርጅት ጽህፈት ቤት መግለጫ የሰጡ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የብሪታኒያ አምባሳደር ማቲው ራይክሮፍት ስለውይይቱ ሲያስረዱ "ኬንያ ዓለም አቀፍ ግዴታዎቿን ማክበር የሚያስፈልጋት መሆኑን አስመልክተን ለኬንያ ፕሬዚደንት እጅግ በጣም ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈንላቸዋል። እንደሚያከብሩም ፕሬዚደንቱ በጣም ግልጽ ባለ መንገድ ቃል ገብተዋል።" ብለዋል።

የኬንያ መንግስት ግዙፉን የዳዳብ የስደተኞች ካምፕ ለመዝጋት ባደረገው ውሳኔ ላይ ለመነጋገር ተባበሩት መንግስታት የጸጥታ ጥበቃ ምክር ቤት ልዑካን በናይሮቢ የአንድ ቀን ጉብኝት አድርገዋል።

በውይይቱ የተደረሰበት አዲስ ርምጃ ባይኖርም ከአንደኛው አምባሳደር እንደተሰማው ግን ኬንያ ጥንቃቄ የጎደለው ግብታዊ ርምጃ አትወስድም።

የጸጥታ ምክር ቤቱ ልዑካን በናይሮቢ ከኬንያ ፕሬዚደንት ኬኒያታ ጋር ከተነጋጋሩ በኋላ የመንግስታቱ ድርጅት ጽህፈት ቤት መግለጫ የሰጡ ሲሆን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የብሪታኒያ አምባሳደር ማቲው ራይክሮፍት ስለውይይቱ ሲያስረዱ "ኬንያ ዓለም አቀፍ ግዴታዎቿን ማክበር የሚያስፈልጋት መሆኑን አስመልክተን ለኬንያ ፕሬዚደንት እጅግ በጣም ጠንካራ መልዕክት አስተላልፈንላቸዋል። እንደሚያከብሩም ፕሬዚደንቱ በጣም ግልጽ ባለ መንገድ ቃል ገብተዋል። " ብለዋል።

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የብሪታኒያ አምባሳደር ማቲው ራይክሮፍት
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የብሪታኒያ አምባሳደር ማቲው ራይክሮፍት

የብሪታንያ አምባሳደር አያይዘው የኬንያ ባለስልጣናት የያዙትን የጸጥታ ጥበቃ ስራ ምክር ቤቱ በአንድ ድምጽ ይገነዘብላቸዋል ብለው ምክር ቤቱ ለመርዳት ዝግጁ ነው ብለዋል።

የጸጥታ ምክር ቤቱ መልዕክተኞች ወደ ናይሮቢ የተጓዙት በሞቃዲሾ የሶማሊያን ፕሬዚደንት፣ ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የካቢኔ አባላት እና ሌሎችንም ካነጋገሩ በኋላ ነው።

ሶማሊያ ለነሃሴ ወር የታቀደውን ምርጫ ሽብርተኝነትን ለመዋጋት እጅግ ጠቃሚ ርምጃ መሆኑን ገልጸውላቸዋል።

XS
SM
MD
LG