በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዑጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሰላማዊ ምርጫ እንደተካሄደ ለሕዝቡ ማረጋገጫ ሰጥተዋል


“እኔ በበኩሌና መንግሥት ሁሉም ለመምረጥ የተመዘገቡት ዜጎች በብዛት ወጥተው የፈለጓቸውን ተወዳዳሪዎችና ፓርቲዎች እንዲመርጡ እናበረታታለን” - የዑጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር

የዑጋንዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ሩሀካና ሩጉንዳ ነገ በሀገሪቱ የሚካሄደው ፕረዚዳንታዊና ምክር ቤታዊ ምርጫ ሰላማዊ እንደሚሆን ለሕዝቡ ማረጋገጫ ሰጥተዋል። ለመምረጥ የተመዘገቡት ዑጋንዳውያን በሙሉ ድምጽ ለመስጠት እንዲወጡ ጥሪ አድርገዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጥሪውን ያቀረቡት በነገው ምርጫ ብጥብጥ ሊኖር ይችላል የሚለውን ስጋት መሰረት በማድረግ ነው። የሚያሰጋ ነገር የለም ሲሉም ሕዝቡን አረጋግተዋል።

“እኔ በበኩሌና መንግሥት ሁሉም ለመምረጥ የተመዘገቡት ዜጎች በብዛት ወጥተው የፈለጓቸውን ተወዳዳሪዎችና ፓርቲዎች እንዲመርጡ እናበረታታለን” ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

የዑጋንዳ ፖሊሶች ትላንት ዋናው ተቃዋሚ ተወዳዳሪ የዲሞክራስያዊ ለውጥ መድረክ የተባለው ፓርቲ መሪ ኪዛ ቤሲጄና ደጋፊዎቻቸው የመጨርሻ የምርጫ ዘመቻ ለማድረግ ሲሞክሩ በአንዳንድ የካምፓላ ክፍሎች ተደራሽነት እንዳያገኙ አግደዋቸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ሩጋንዳ ታድያ ድርጊቱ ያሳዝናል ካሉ በኋላ ቤሲጄና ደጋፊዎቻቸውም ቢሆኑ በካምፓላ የቢዝነስ ወረዳ ዘመቻ ማካሄድ አልነበረባቸውም ሲሉ አስገንዝበዋል።

XS
SM
MD
LG