በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አወዛጋቢው የዑጋንዳ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወደ ፍርድ ቤት ሊያመራ ነው


“የምርጫው ዘመቻዎቹ መካሄድ ከጀመሩበት ጊዜ አንስቶ ከሰማኒያ በላይ የሚሆኑ በመገናኛ ብዙሃን መብትና ነጻነት ላይ የተነጣጠሩና የተቃጡ ጥሰቶችን መዝግበናል። በአብዛኛውም በጸጥታ ኅይሎች፤ በተለይም ደግሞ ከጦር ሠራዊቱ ጋር እጅና ጓንት ሆኖ በመስራት ላይ በሚገኘው የአገሪቱ ፖሊስ ነው የተፈጸሙት።” Robert Ssempala የዑጋንዳ ጋዜጠኞች የሰብዓዊ መብት ማኅበር አባል።

ዑጋንዳ የየካቲት አሥሩን ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ አወዛጋቢ ውጤት ተከትሎ በአገሪቱ የነገሰው ውጥረት እየናረባለበት ባሁኑ ወቅት፤ ጉዳዩ ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሊያመራ መሆኑ ተገለጠ።

ከፕሬዝዳንታዊ ተፎካካሪዎች የአንዱ የAmama Mbabazi ነገረ ፈጅ ናቸው፤ በትላንትናው እለት ከጊዜ ገደቡ ማብቂያጥቂት ደቂቃዎች ቀደም ብለው የክስ አቤቱታውን ለአገሪቱ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ያስገቡት።

የክስ አቤቱታው፥ ጉቦን፥ የድምጽ መስጫ ቁሳቁሶች ከተመደበላቸው ጊዜ ዘግይቶ መድረስና “የምርጫ ካርዶች አስቀድመውከተለዩ በኋላ በኮሮጆዎች ታጭቀው ተወስደዋል፤” የሚለውን ጨምሮ ሃያ ስምንት የተለያዩ ክሶችን ነው ተቃዋሚዎችያቀረቡት።

የዑጋንዳ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የMr Mbabazi’ን ጉዳይ በሚቀጥለው ሳምንት ይመለከታል ተብሎ ይጠበቃል። ብይንለመስጠትም የሰላሳ ቀናት እድሜ አሉት።

አወዛጋቢው የዑጋንዳ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ወደ ፍርድ ቤት ሊያመራ ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:39 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG