በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዑጋንዳ መንግስት ለኤልኒኞ እየተሰናዳ ነው


ዑጋንዳ በኤልኒኞ ሳቢያ ሊከተል የሚችለውን እጅግ ከባድ ጎርፍና የመሬት ናዳ ለመቋቋም እየተሰናዳ መሆኑን መንግስት ይፋ አድርጓል።

በኢልኒኞ የዓየር ጠባይ ለውጥ የተመታው የምሥራቅ አፍሪቃና አካባቢው አገሮች ክስተቱ ሊያስከትል የሚችለውን አደጋ ለመቀነስና ለመከላከል የሚያግዙ ዝግጅቶችን በማድረግ ላይ መሆናቸው እየተዘገበ ነው።

ገዳይ በሆነ የኮሌራ ወረርሽኝ በተጠቃችው ዑጋንዳ በኤልኒኞ ሳቢያ ሊከተል የሚችለውን እጅግ ከባድ ጎርፍና የመሬት ናዳ ለመቋቋም እየተሰናዳ መሆኑን መንግስት ይፋ አድርጓል።

በደሳሳ ጎጆዎችና በተፋፈጉ የከተማ ቀዬዎች የሚኖሩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ለከፋው አደጋ ይበልጥ የተጋለጡ መሆናቸውንም ከካምፓላ የደረሰን ዘገባ ያስረዳል።

XS
SM
MD
LG