በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በብራስልስ ስለ ደረሰው ጥቃት የሁለት ኢትዮጵያውያን አስተያየት


የብራስልስ ከተማ ትናንት ማለዳ በሦስት ፍንዳታዎች ተመታች፣ በአደጋውም 34 ሞተው ከ130 በላይ ቆሰሉ። ከሦስቱ ፍንዳታዎች ሁለቱ በባቡር ጣቢያ፣ አንዱ ደግሞ ዋና ከተማዋ እምብርት ላይ በሚገኘው የባቡር ጣቢያ ነው የደረሱት።

"የዛሬው ቀን ለአገራችን የጨለማ ወቅት ነው" ያሉት የቤልጅግ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ቻርልስ ሚሸል (Charles Michel) ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ሁናቴ ነው፣ ሕዝባችን እንዲረጋጋና መንፈሰ-ጠንካራ እንዲሆን ጥሪ የማቀርበው ብለዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆኑ ዐቃቤ ህጉ ፍረዴሪክ ቫን ሊው አንደኛውን ፍንዳታ ያደረሰው አጥፍቶ-ጠፊ መሆኑን ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት ኩባን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት የዩናትድ ስቴትሱ ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማም ከሀቫና ባስተላለፉት መልዕክት፣ በደረሰው አደጋ ኃዘናቸውን ገልጸው፣ "እነዚህን የጥፋት መልዕክተኖች እገቡበት እየገባን ለፍርድ በማቅረብ፣ በዚህ እረገድ ለቤንጂግ ወዳጃችን የምንችለውን ሁሉ እናደርጋለን" ብለዋል።

ብራስልስ ከተማ ውስጥ ማክሰኞ ማለዳ በደረሱ ሦስት ፍንዳታዎች ቢያንስ 34 ሰዎች ሞተው ሌሎች 130 መቁሰላቸው ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:01 0:00

በዚሁ ጉዳይ አዲሱ አበበ ወደ ብራስልስ ደውሎ ሁለት ኢትዮጵያውያንን አነጋግሯል። አቶ ያሬድ ኃይለማራም እና አቶ ሰሎሞን መኩሪያ ይባላሉ። ዝርዝሩን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያድምጡ።

በብራስልስ ስለ ደረሰው ጥቃት የሁለት ኢትዮጵያውያን አስተያየት
please wait

No media source currently available

0:00 0:08:43 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG