በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሁለት ኢትዮጵያውያን ከ30,000 ዶላር በላይ ለዓለም ምግብ ፕሮግራም አስረከቡ

ሁለት ኢትዮጵያውያን ዳያስፖራ ከ30,000 ዶላር በላይ የምግብ እጥረት ለደረሰባቸው ወገኖች እርዳታ ሰብስበው በዛሬው እለት ገንዘቡን ለዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ለተራቡ ወገኖች እንዲያደርስ አስረክበዋል። ጎ-ፈንድ-ሚ ወይም (GoFundMe) በግርዱ ወደ አማርኛ ሲመለስ፤ “ድጋፍህን ስጠኝ፤” በሚል ስያሜ በሚታወቀውና በሚልዮኖች የሚቆጠሩ ሰዎች ከ1 ቢልዮን ዶላር በላይ በ 365 ቀናት ውስጥ ሊሰበስቡ የሚችሉበት ድረ-ገጽ ነው።

ሁለት ኢትዮጵያውያን፣ ዶ/ር አበበ ሃረገውይንአብርሃም ተፈሪ ጎ-ፈንድ-ሚ ወይም (GoFundMe)ን ድረ-ገጽ በመጠቀም በአሁኑ ጊዜ ኢትዮጵያ ውስጥ የምግብ እጥረት ለደረሰባቸው ወገኖች እርዳታ አሰባስበዋል። እስከ ዛሬ ከ30,000 ዶላር በላይ የሰበሰቡ ሲሆን፣ በዛሬው እለት ገንዘቡን ለዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ለተራቡ ወገኖች እንዲያደርስ አስረክበዋል። ሳሌም ሰለሞን በርክክቡ ላይ ተገኝታ ያነሳቻቸውን የፎቶ መድብሎች ይመልከቱ።


ተጨማሪ ይጫኑ

XS
SM
MD
LG