በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያ ክልል ዋትስ አፕ እና ትዊተር መስራት ካቆሙ ከአንድ ወር በላይ መሆኑን ብሉምበርግ ዘገበ


ስማርትፎን ስልኮች ያሏቸው ሰዎች በሀገሪቱ ብቸኛው በሆነው በመንግስቱ ኢቲዮቴሌኮም የፌስቡክም ሆነ የትዊተር መልዕክት አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን ወሊሶ ከተማ የዩኒቨርስቲ መምህር ስዮም ተሾመ መናገራቸውን ብሉምበርግ ጠቅሷል።

በተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች በቅርቡ የሰዎች ህይወት የጠፋባቸው የተቃውሞ እንቅስቅሴዎች የተካሄዱበትን የኦሮሚያን ክልል ጨምሮ ዋትስ አፕን (WhatsApp) የመሳሰሉ የኢንተርኔት የጽሁፍ መልእክት መላላኪያዎች መስራት ካቆሙ ከአንድ ወር በላይ መሆኑን ብሉምበርግ የአገር ውስጥ ተጠቃሚዎችን ጠቅሶ ዘገበ።

ስማርትፎን ስልኮች ያሏቸው ሰዎች በሀገሪቱ ብቸኛው በሆነው በመንግስቱ ኢቲዮቴሌኮም የፌስቡክም ሆነ የትዊተር መልዕክት አገልግሎት ማግኘት አለመቻላቸውን ወሊሶ ከተማ የዩኒቨርስቲ መምህር ስዮም ተሾመ መናገራቸውን ብሉምበርግ ጠቅሷል

የትዊተር ኩባኒያ ቃል አቀባይ በጉዳዩ ላይ አስተያየት ለመስጠት ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን ከሁለት ዓመታት በፊት ዋትስአፕን የገዛው ፌስቡክ ኩባኒያም እስካሁን ምላሽ እንዳልሰጠ ነው ዘገባው ያመለከተው።

በኦሮሞ ብሄረሰብ አባላት ሲካሄድ በቆየው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ላይ የመንግስት የጸጥታ ሃይሎች በወሰዱት የጥቃት ርምጃ ቢያንስ 266 ሰዎችን ገድለዋል ሲል ጽህፈት ቤቱ ኬንያ የሚገኝ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ፕሮጄክት ባለፈው መጋቢት ያቀረበውን ሪፖርት ጠቅሶ የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ የጸጥታ አባላትን ጨምሮ ብዛት ያላቸው ሰዎች ሞተዋል በማለት አክሏል።

ዩናይትድ ስቴትስ ያሉ ጃዋር መሃመድ የተባሉ የማህበራዊ መገናኛ አክቲቪስት ስለኦሮሚያ የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ከ500,000 ለሚበልጡ የፌስቡክ ተከታዮቻቸው መረጃና ቪዲዮ ሲያስተላልፉ መቆየታቸውን ዘገባው አመልክቷል።

ብሉምበርግ ስለጉዳዩ የጠየቃቸው የኢትዮጲያ መንግስት ቃል አቀባይ ጌታቸው ረዳ አገልግሎት መከልከል የመንግስታችን ፖሊሲ አይደለም ብለው የኮኔክሺን ወይም የመገናኛ መስመር መቆራረጥ ሊሆን ይችላል ገና የችግሩን ምክኒያት አልደረስንበትም ማለታቸውን አውስቷል።

ቢሮው ኒውዮርክ የሆነው ሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ክፍል ምክትል ድሬክተር ሌስሊ ሌፍኮ የመናገር ነጻነትን መገደብ የመረጃ አገልግሎትን መከልከል በኢትዮጲያ መንግስት ባለስልጣናት የተለመደ አድራጎት ነው። ስለኦሮሞዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ዜናና መረጃ።

የሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ክፍል ምክትል ድሬክተር ሌስሊ ሌፍኮ /ፋይል ፎቶ/
የሂዩማን ራይትስ ዋች የአፍሪካ ክፍል ምክትል ድሬክተር ሌስሊ ሌፍኮ /ፋይል ፎቶ/

እንዳይወጣ የመህበራዊ መገናኛውን መስመር ቢቆርጡት የሚጠበቅ ተግባር ነው ማለታቸውን ብሉምበርግ ጠቅሷል።

ኢትዮ ቴሌኮም የነፃ የስልክ ጹሑፍ መልዕክትን ጨመሮ፤ ለቫይበር፣ ዋትስ አፕ፣ ዊቻና የመሳሰሉት አፕሊኬሽኖች ተጨማሪ ክፍያ የሚያስክፈል፤ አስፈላጊ ኾኖ ከተገኘ ደግሞ እነዚህን አፕሊኬሽኖች የሚዘጋ (ውይም ብሎክ የሚያደርግ)አዲስ ቴክኖሎጂ ሀገር ውስጥ ማስገባቱን ባለፈው ሳምንት የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አንዱአለም አድማሴን ባነጋገርንበት ወቅት አስታውቋል፡፡

XS
SM
MD
LG