በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

"ጉዞው ለአሜሪካ ትልቅ ስኬት አስመዝግቧል"-ፕሬዚዳንት ትራምፕ


የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ተለመደው የዋሺንግተኑ ሕይወታቸው ተመልሰው ዋይት ሃውስ እየታመሰ ስላለበት የእሳቸው ረዳቶችና የሩስያ ግንኙነት በተመለከተ በሚካሄዱት ምርመራዎች የሚወጡ የዜና ዘገባ መጨፍጨፋቸውን ተያይዘውታል።

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት ዶናልድ ትራምፕ ወደ ተለመደው የዋሺንግተኑ ሕይወታቸው ተመልሰው ዋይት ሃውስ እየታመሰ ስላለበት የእሳቸው ረዳቶችና የሩስያ ግንኙነት በተመለከተ በሚካሄዱት ምርመራዎች የሚወጡ የዜና ዘገባ መጨፍጨፋቸውን ተያይዘውታል።

ፕሬዚዳንት ለዘጠኝ ቀናት ከከረሙበት የመካከለኛው ምሥራቅና የአውሮፓ ጉብኝት በተመለሱበት በዛሬው የመጀመሪያ ቀናቸው

“ጉዞው ለአሜሪካ ትልቅ ስኬት አስመዝግቧል። ከባድ ሥራ፣ ሆኖም ታላላቅ ውጤቶች” ሲሉ በትዊተር ፅፈዋል።

ያን ካሉ በኋላ ፈጥነው በብዙኀን መገናኛ ላይ ወደ አሏቸው ብሶቶች ተመልሰዋል።

“እንደኔ አስተያየት ከዋይት ሃውስ በድብቅ እየሾለኩ የሚወጡት ብዙ ወሬዎች በውሸት ዜና ማሰረጫው

“ፌክ ኒውስ” ወይንም “የሃሰት ወሬ ነው” የሚፈበረክበት ብለዋል።

በሃሰት ዜና መገናኛ ብዙሃኑ “ምንጮቻችን እንዳሉት ብለው ስም ሳይጠቅሱ የሚወጡ ወሬዎችን ከአያችሁ ምንጮች የተባሉት የሌሉ ነገር ግን በውሸት ዜና ፀሐፊዎች የፈጠሩዋቸው ሊሆኑ ይችላሉ። ጠላት የውሸት የመገናኛ ብዙሃን!” ብለዋል።

አክለውም ፕሬዚዳንቱ በትዊተር ስለመጠቀማቸው ሲሟገቱ በማኅበራዊ መገናኛ ስለመጠቀም መገናኛ ብዙሃኑ መሳለቂያ ማሾፊያ ሊያደርግ ይለፋል። ለምን አሜሪካውያን ዕውነቱን እንዲሰሙ ስለማይፈልግ ነው” ብለዋል።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ እና የዋይት ሃውስ ቤተ መንግሥት አማካሪዎቻቸው በምርጫ ዘመቻው ወቅትና በኋላም ከሩስያ ባለሥልጣናት ጋር ፈጥረዋል ስለተባለው ግንኙነት ለወራት የሚዘልቅ ምርመራ ተደቅኖባቸዋል።

ከዚያም በላይ ትራምፕ የፍትሕ ሂደት ሊያደናቅፉ እና ምርመራዎቹ እንዲቋረጡ ለማድረግ ሞክረዋል ብለው ተቃዋሚ ዲሞክራቶች ወንጅለዋቸዋል።

የፕሬዚደንት ትረምፕ አማካሪዎች የሩስያ ባለስልጣናት በኅዳሩ ምርጫ በሕገ ወጥ መንገድ እንዲረዷቸው ተመሳጥረዋል በተባለው ውንጀላ ዙሪያ በልዩ ዓቃቤ ሕግ ምርመራ እየተካሄደ ሲሆን የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤታዊ ኮሚቴዎች ደግሞ በርካታ የፕሬዚዳንቱ የቀድሞ እና የአሁን ረዳቶቻቸው ቀርበው ቃላቸውን እንዲሰጡ ጠይቀዋል።

ፕሬዚደንት ትራምፕ ከሥራ ያባረሩዋቸው የቀድሞ የፌዴራል ምርመራ ቢሮ ዳይሬክተር ጄምስ ኮሚ ለምክር ቤቱ ስለሚሰጡት የምስክርነት ቃልም ዋይት ሃውስ በሥጋት ላይ ነው።

ትራምፕ ሚስተር ኮሚን ከማባረራቸው በፊት በቀድሞው የብሔራዊ ፀጥታ አማካሪያቸው ማይክል ፍሊን እና የሩስያ ክሬምሊን ቤተ መንግሥት ግንኙነታቸው ላይ የተጀመረውን ምርመራ እንዲያቆሙ ጠይቀዋቸዋል ተብሉዋል።

አሁን ደግሞ አዲሱ የምርመራ ትኩረት የሆኑት ከፕሬዚዳንት ትራምፕ የቅርብ አማካሪዎች አንዱ

አማቻቸው ጃረድ ኩሽነር ናቸው።

ትራምፕ ውጭ ሃገር ጉብኝት ላይ ባሉበት “ዘ ዋሽንግተን ፖስት” ጋዜጣ ባወጣው ዘገባ ጃሬድ ኩሽነር በዋሺንግተን የሩስያ አምባሳደር ሰርጌይ ኪስሊያክ ጋር ተገናኝተው ከሞስኮ ጋር በሚስጥር መነጋገሪያ መሥመር ለማስከፈት ሞክረዋል ብሉዋል።

በዘገባው መሠረት ኩሽነር ይህን ያደረጉት ትራምፕ ከተመረጡ በኋላ ሆኖ ነገር ግን ባራክ ኦባማ ከመሰናበታቸው በፊት ነው።

የጀረድ ኩሽነር ጠበቆች ለመርማሪዎች ቃላቸውን ለመስጠት ፈቃደኛ ናቸው ብለዋል።

የፌስቡክ አስተያየት መስጫ

XS
SM
MD
LG