በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አል-ሸባብ በጋሪሳ ላይ የፈጸመው ጥቃት ቅዳሜ አመት ሊሆነው ነው


ፋይል ፎቶ -አል-ሸባብ በጋሪሳ ላይ ጥቃት በፈጸመበት ወቅት የተነሳ ፎቶ
ፋይል ፎቶ -አል-ሸባብ በጋሪሳ ላይ ጥቃት በፈጸመበት ወቅት የተነሳ ፎቶ

ኬንያ በሚገኘው ጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ላይ የተፈጸምው የአሸብሪዎች ጥቃት በመጪው ቅዳሜ አንድ አመት ይሆነዋል። የዐል ሸባብ አማጽያን በዩኒቨርሲቲው በከፈቱት ጥቃት 148 ሰዎች ተገድለዋል። አብዛኞቹ ተማሪዎች ነበሩ። ኬንያ ለእንደዚህ አይነት ጥቃት ምላሽ የመስጠት ብቃትዋን እንዳጠናከረች ገልጻለች።

አምና እ.አ.አ. ሚያዝያ ሁለት ቀን ላይ አራት የአል-ሸባብ አማጽያን በሰሜን ኬንያ በሚገኘው ጋሪሳ ዩኒቨርሲቲ ላይ ወረራ ፈጸሙ። የ 22 አመት እድሜ ወጣት ስቲቭ ምዋንጋ እዛው ነበር። ከሌሎች ሶስት ተማሪዎች ጋር ሆኖ ቁም ሳጠን ውስጥ ተደበቁ።

“ከንጋቱ አንድ ሰዓት አንስተን እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ተደብቀብ ዋልን። ከዚያ እኛን ለማትረፍ ስኳድ ወደ ሆስቴሉ መጣ። ከዛ ቦታ እምወጣ መስሎ አልተሰማኝም ነበር። ሰዎችን ይገድሉ ስለነበርና አብረውኝ የሚማሩ ሁለት ልጆች መገደላቸውን ሳይ ቀጥሎ እኔን ነው የሚገድሉት የሚል ስጋት አድሮብኝ ነበር። እንደ እድል ሆኖ ግን አልገደሉኝም።”ብሏል።

በአሁኑ ወቅት ከዩኒቨርሲቲው መኝታ ቤት ወጥቶ እየተመላለስ ነው የሚማረው። በድጋሚ ጥቃት እንዳይከፈት በመስጋት እዛ እንደማያድር ገልጿል።​

​አል-ሸባብ በዩኒቨርሲቲው ላይ ጥቃት የከፈተው ኬንያ በሶማልያ የምታካሄደውን ወታደራዊ እንቅስቅሴን ለመበቀል ነው ይላል።

አማጽያኑ ጋሪሳን ቢያንስ ለ 12 ሰዓታት ያህል ይዘዋል። 148 ሰዎች ተገድለው ብዙ ቆስለዋል። የሚድያ ዘገባዎች እንደሚሉት የኬንያ የጸጥታ ሃይሎች በቦታው ለመድረስ ቢያንስ ሰባት ሰዓት ፈጅቶባቸዋል። በመዘግይተውም ክፉኛ ተነቅፈዋል።

የናይጄርያ የአገር አስተዳደር ሚኒስትር ምዌንዳ ንጆካ ጉድለቶችን አስተካክለናል ብለዋል።

“ሄሊኮፕተሮቹ ስለታደሱና አዲሶችም ስለተገዙ እግረኛ ወታደሮቻችን በፍጥነት ለመንቀሳቀስ ችለዋል። የጋሪሳ ዩኒቨርሲትን በሚመልከት በሚገባው ፍጥነት እንዳልደረስን ሁሉም አምኖ ተቀብሏል። ይሁንና አሁን ያለን መሳርያ ያኔ ኖሮን ቢሆን ኖሮ በአንድ ሰአት ውስጥ ለመድረስ በቻልን ነበር።”ብለዋል

የጸጥታ ተንታኞች በበኩላቸው አሁንም ቢሆን ጥቃት ሊደርስ የሚችልበት ሁኔታ እንዳለ አስገንዝብዋል። የአገር ውስጥ ደህንነት ባለሙያ ሪቻርድ ቱታ በጋሪሳ የደረሰውን ጥቃትና በምዕራብ አፍሪቃ ሆቴሎች የተከሰቱትን ጥቃቶች ለመፈጸም የሚያስፈልጉት እፍኛ የማይሞሉ አማጽያን ናቸው ብለዋል።

“ከፈተኛ ጉዳት ሊደርስ ይችላል። እንዲህ አይነቶቹን ኢላማ ለመምታት ብዙም ዝግጅት ስለ ማያስፈልግ ዝቅጠኛ ዋጋን ነው የሚያስከፍለው።”ብለዋል።

አል-ሸባብ በጋሲሳና ከሁለት አመታ በበፊት ደግሞ በዌስትጌት የገበያ ማዕከል ላይ የፈጸማቸው ጥቃቶች ለፕሮፓጋንዳ ጠቅመውታል። ይሁንና ከአምና አንስቶ ዐል-ሸባብ በጋሪስ ላይ ጥቃት በከፈተበት ወቅት በሶማልያ ያለው የአፍሪቃ ህብረት የሰላም ጥበቃ ተልእኮ በሚያደርስበት ጫና ምክንያት የተዳከ መስሎ ነበር የተታየው። ይሁንና ከአምና አንስቶ በሶማልያ ያሉትን ወታደራዊ ሰፈሮች ወሮ ቢያንስ በሁለት ጥቃቶች የሰላም ጥበቃ ተልእኮ ወታደሮችን ለመግደል ችሏል። ሶማልያ ውስጥ የቦምብ ጥቃቶችን አበራክቷል።

አንዳንድ ጠበብት እንደሚሉት እስላማዊ መንግስት ነኝ የሚለው ቡድን የአል ሸባብ አማጽያንን እየሳበና አዲሶችንም እየመለመለ በመሆኑ ከዓል-ቓዒዳ ጋር የተሳሰረው አል-ሸባብ ለህልውናው እየተፍጨረጨረ ሳይሆን አይቀርም።

ናይሮቢ ያሉ የጸጥታ ጉዳይ ባለሙያ አንድሪው ፍራንክሊን በበኩላቸው አል-ሸባብ በሀገሪቱ የሚካሄደውን ምርጫ የማሰናከል አላማ እንዳለው ጠቁሟል።

“የአል-ሸባብ አላማን ትልቁ ስእል አላስተዋልንም። አል-ሸባብ በዚህ አመት ትኩረት የሚሰጠው ጉዳይ በመጪው ነሀሴ ወር ሊካሄድ የታቀደውን ምርጫ ማሰናከል ነው። አላማው የሶማልያ ፌደራላዊ መንግስት ምርጫ ለማካሄድ እንደማይችል ማሳየት ነው።”ብለዋል።

ኬንያ ከጋሪሳ ወዲህ ትልቅ የሽብር ጥቃት አልደረሰባትም። ይሁንና አደጋው እንዳለ ነው። የአፍሪቃ የጸጥታ ጥበቃ አገልግሎቶች ጽንፈኛ ቡድኖችን ለመከለክልና ወጣቶችን በመበከል ላይ ያለው ጽንፈኛ ርእዮተ-አለም እንዳይስፋፋ ለማስቆም አብረው መስራት እንዳለባቸው የጸጥታ ጠበብት ይመክራሉ።

ክልሉና በአጠቃላይ አህጉሪቱ ለተመሳሳይ ጥቃቶች በተጠንቀቅ ላይ እንደሚገኙ ዘጋብያችን መሐመድ ዮሱፍ ከናይሮቢ በላከው ዘገባ ጠቅሷል አዳነች ፈሰሀየ አቅርባዋለች፣ ከድምጽ ፋይሉ ያድምጡ።

አል-ሸባብ በጋሪሳ ላይ የፈጸመው ጥቃት ቅዳሜ አመት ሊሆነው ነው
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:41 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG