በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ማዕቀቦቹ እንዲሠሩ ኢትዮጵያ ትገፋለች


በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሣደር ዶ/ር ተቀዳ ዓለሙ
በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሣደር ዶ/ር ተቀዳ ዓለሙ

ኤርትራ ውንጀላዎቹን ውድቅ እያደረገች ማዕቀቦቹን ታወግዛለች፡፡

በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ በሚገባ ተግባራዊ እንዲደረግ መንግሥታቸው ግፊት ማድረጉን እንደሚቀጥል በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሣደር ዶ/ር ተቀዳ ዓለሙ ለቪኦኤ ገልፀዋል፡፡

በአፋር ክልል በቱሪስቶች ላይ ከደረሰው ጥቃት በኋላ የኢትዮጵያና የኤርትራ ጉዳይ የመገናኛ ብዙኃንን ትኩረት ይበልጥ ስቧል፡፡

ጥቃቱን ያደረሱትና አምስት አውሮፓዊያንን ገድለው ሦስቱን ያቆሰሉት፣ ሁለቱን ደግሞ ያገቱት በኤርትራ የተላኩ ኃይሎች ናቸው ሲል የገለፀው የኢትዮጵያ መንግሥት ትዕግሥቱ እየተሟጠጠ መሆኑንም አስታውቋል፡፡

ከዚህ አንፃር በኤርትራ ላይ የተጣሉት ማዕቀቦች በሚገባ ተግባራዊ መደረግ እንዳለባቸውም በማሰብ ላይ ይገኛል፡፡ በአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ላይ ለመገኘት አዲስ አበባ ያሉት በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ አምባሣደር ለቪኦኤ ሲናገሩ ይህንኑ አቋም አንፀባርቀዋል፡፡

የሚተላለፉ የማዕቀብ ውሣኔዎች በሚገባ ተግባራዊ መደረግ እንዳለባቸው የተናገሩት ዶ/ር ተቀዳ ዓለሙ እስከአሁን ግን ይህ ሲሆን እንዳልታየ ጠቁመዋል፡፡

በኤርትራ ላይ ሁለተኛው ውሣኔ የተላለፈውም የመጀመሪያው በሚገባ ተግባራዊ ባለመደረጉ ጭምር እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

የኤርትራ መንግሥት የሚሠነዘሩበትን ክሦች ሁሉ እያስተባበለና የተጣሉበትንም ማዕቀቦች እያወገዘ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ዶ/ር ተቀዳን አዲስ አበባ ላይ ያነጋገረውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG