በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሜቄዶኒያ ግሪክ ድንበር በኩል በፍልሰተኞች ላይ የተጀመረው ውጥረት አሁንም እንደጋመ መሆኑ ተሰማ


ዛሬም ብዛት ያላቸው ፍልሰተኞች በድንበር አጥሩ በግሪክ በኩል ተሰባስበዋል። ግጭት ስለመከሰቱ የተሰማ ዘገባ ግን የለም።

የሜቄዶኒያ ፖሊሶች ከግሪክ ድንበር በኩል አጥር ሰብረው ሊገቡ በሞከሩ ብዙ መቶ ፍልሰተኞች ላይ አስለቃሽ ጋዝና የጎማ ጥይት በተኮሱበት የስደተኞች ካምብ ኢዶሚኒ፣ ውጥረቱ አሁንም እንደጋመ መሆኑ ተሰማ።

ዛሬም ብዛት ያላቸው ፍልሰተኞች በድንበር አጥሩ በግሪክ በኩል ተሰባስበዋል። ግጭት ስለመከሰቱ የተሰማ ዘገባ ግን የለም።

የህክምና በጎ አድራጎት ድርጅቶች ሲናገሩ በትናንቱ ግችት የተጎዱ ወደ ሶስት መቶ የሚሆኑ ሰዎች ታክመዋል። የሚበዙት በአስለቃሽ ጋዙ ምክንያት የመተንፈስ ችግር የደረሰባቸው ሲሆኑ በጎማ ጥይት የቆሰሉም እንዳሉ ገልጸዋል።

የሜቄዶኒያ ባለስልጣናት በበኩላቸው ሃያ ሶስት የጸጥታ ጥበቃ አባላት ከተቃዋሚዎች በተወረረ ድንጋይ ቆስለዋል ይላሉ። ሜቄዶኒያ ድንበሯን ልትከፍተው ነው የሚል ወሬ በመሰማቱ በአኢዶሜኒ መጠለያ ካምፕ ውጥረቱ ተባብሱዋል።

የባልካን ሃገሮች ድንብሮቻቸውን ከዘጉበት ካለፈው የካቲት ወዲህ በሰሜናዊ ግሪክ በሚገኘው ኢዶሜኒ የድንበር መቁዋረጫ ላይ ከአስር ሺህ በላይ ፍልሰተኞች ማለፊያ አጥተዋል።

XS
SM
MD
LG