በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሩሲያ የታገዙ የሦሪያ ወታደሮች፥ ሦርያን ከእስላማዊ መንግሥት ነውጠኞች የማጽዳት ዘመቻቸው ቀጥሏል


የአካባቢው ባለሥልጣናትና የሦሪያ የሰብዓዊ መብቶች ቃፊር እንደገለጹት፥ የመንግሥቱ ኃይሎች ወደ ከተማይቱ ደቡባዊና ምዕራባዊ ጠርዝ ተቃርበዋል።

በሩሲያ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች የታገዙ የሦሪያ ወታደሮች፥ አካባቢውን ከእስላማዊ መንግሥት ነውጠኞች አጽድተው ለመቆጣጠር በከፈቱት ዘመቻ፥ ወደ ጥንታዊቷ ፓልሚይራ (Palmyra) ከተማ እየገሰገሱ ነው።

የአካባቢው ባለሥልጣናትና የሦሪያ የሰብዓዊ መብቶች ቃፊር እንደገለጹት፥ የመንግሥቱ ኃይሎች ወደ ከተማይቱ ደቡባዊና ምዕራባዊ ጠርዝ ተቃርበዋል።

እራሡን እስላማዊ መንግሥት ነኝ ብሎ የሚጠራው ቡድን አካባቢውን የተቆጣጠረው ባለፈው ዓመት ግንቦት እንደነበር ሲታወስ፥ ተዋጊዎቹ ዩኔስኮ (UNESCO)የዓለም ቅርስ ሲል በሰየመው ሥፍራ የሚገኘውንና በሮማውያን ክፍለ ዘመን የታነጸውን ታሪካዊ ሐውልት ማውደማቸው ዓለምአቀፉን ህብረተሰብ አስቆጥቷል።

የዩኔስኮ (UNESCO) ኃላፊ ኢራና ቦኮቫ (Irna Bokova) ይህንኑ አስመልክተው ሲናገሩ፥ ”እስላማዊ መንግሥት ነኝ ባዩ ጽንፈኛ ቡድን፥ ታሪክና ባህል ቢያስደነግጠውም፥ ተዋጊዎቹ ታሪክን ማጥፋት ግን ፈጽሞ አይችሉም” ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ በዩክሬን እና ሦሪያ የቀውስ ሁኔታዎች ላይ እየተወያዩ ነው

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ የዩናይትድ ስቴትሱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ (John Kerry) ደግሞ በክሬምሊን ቤተ መንግሥት በዩክሬን እና ሦሪያ የቀውስ ሁኔታዎች ላይ ከሩሲያው ፕሬዘዳንት ቭላድሚር ፑቲን (Vladimir Putin) እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሰርጌ ላቫሮቭ (Sergei Lavrov) ጋር ለመነጋገር ሞስኮ ይገኛሉ።

መሪዎቹ፥ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኬሪ (Kerry)”በቤልጂግ ሕዝብና ባጠቃላይ በአውሮፓ ላይ የተቃጣ ነው” ሲሉ ስለገለጹት፥ ስለ ትላንቱ አሸባሪዎች በብራሰልስ ስላደረሱት ጥቃትም ሊወያዩ ይችላሉ ተብሏል።

አንድ ከሚስተር ኬሪ ጋር በጉዞ ላይ ያሉ ከፍተኛ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ባለሥልጣን ለጋዜጠኞች ሲናገሩ፥ ጆን ኬሪ የብራሰልሱን ጥቃት የሚያዩት፥ የነውጠኛው እሥላማዊ መንግሥት ቡድን ከጋረጠው አጠቃላይ ስጋት ጋር ነው ብለዋል። በቤልጂግ ዋና ከተማ ውስጥ ለደረሱት ፍንዳታዎች፥ ቡድኑ ኃላፊነት ወስዷል።

XS
SM
MD
LG