በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የስዊድናዊያኑ ጋዜጠኞች የችሎት ውሎ


ስዊድናዊያኑ ጋዜጠኞች ዛሬ፣ ማክሰኞ ጥቅምት 21/2004 ዓ.ም ችሎት ቀርበዋል፡፡

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሦስተኛ ወንጀል ችሎት በሁለቱ ስዊድናውያን ጋዜጠኞች እና ሁለት የኦብነግ ታጣቂዎች በተባሉ ተከሣሾች ላይ አቃቤ ህግ ያቀረባቸውን ምስክሮች አደምጧል፤ የቪዲዮ ማስረጃዎች ተመልክቷል።

ችሎቱ ለነገ ረቡዕ፤ ጥቅምት 22/2004 ዓ.ም ጠዋት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

ስዊድናዊያኑ ጋዜጠኞች ተገቢውን የጉዞ ሠነድ ሳንይዝ ድንበር ጥሰን በመግባታችን ጥፋተኞች ነን በማለት የኢትዮጵያ መንግሥትን ይቅርታ መጠየቃቸው ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ "በሽብርተኝነት ተግባር የቀረበብን ክስ ያላደረግነው በመሆኑ አንቀበለውም፥ በስፍራው የተገኘነው 'በአካባቢው አለ' በተባለው ግጭት ላይ ዘገባ ለማቅረብ ነው ማለታችው አይዘነጋም።

የፍርድ ሂደቱ የዓለምአቀፍ አካላትን ትኩረት ስቧል።

ዝርዝሩን ከመለስካቸው አምሃ ዘገባ ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG