ዋሽንግተን ዲሲ —
ቻይና ውስጥ የታዋቂው የመብት ተሟዋጋች ጠበቃ ፑ ዢኪያንግ የፍርድ ሂደት በተካሄደበት የቤጂንግ ፍርድ ቤት ደጃፍ ጥቂት ደጋፊዎቹ ተሰባስበው ድጋፋቸውን ገልጸዋል።
ታዋቂው የምብት ተሟዋጋች ፑ ዢኪያንግ
የሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋዜጠኞችን ተቃዋሚ ሰልፈኞችንና የውጭ ዲፕሎማቶች ላይ ወከባ ሲያካሂዱ ቢስተዋልም የጠበቃው ደጋፊዎች በስፍራው ተገኝተው ድጋፋቸውን ከመግለጽ ወደኋላ እንዳልላሉ ዜናው ጠቁሟል።
ጠበቃ ፑ ዢኪያንግ የቻይናን ኮሙኒስት ፓርቲና ፖሊሲዎቹን ነቅፎ በማህበራዊ መገናኛ ላይ በማውጣቱ እስከስምንት ዓመት የሚደርስ እስራት ሊፈረድበት ይችላል።