በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የተቃውሞ ሰልፎች በኦሮሚያና በውጭ አገሮች ከተሞች፥ ግጭቶችና አማራጮች


በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎች መሰንበቻውን በማካሄድ ላይ ያሏቸው የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ዛሬም ቀጥለዋል።

በኦሮምያ ክልል የተለያዩ ከተሞች የሚገኙ ትምሕርት ቤቶች ተማሪዎች መሰንበቻውን በማካሄድ ላይ ያሏቸው የተቃውሞ እንቅስቃሴዎች ዛሬም ቀጥለዋል።

በዛሬዎቹ ሰልፎች ወቅት በአንዳንድ አካባቢዎች የተገደሉ ሰዎች መኖራቸውን ለአሜሪካ ድምጽ የተናገሩ አንዳንድ የአካባቢዎቹ ነዋሪዎችና በአካባቢዎቹ የሚንቀሳቀሰው የኦሮሞ ፌድራሊት ኮንግሬስ አመራሮች ተናግረዋል።

የአገራችን ሕገ መንግስት በግልጽ እንዳስቀመጠው ክልሎች የራሳቸውን ሕግ ያወጣሉ። ይሄ ሕግ የወጣው ኦሮምያ ክልል ከተሞች ላይ ነው እንጂ ከማስተር ፕላኑ ጋር ግንኙነት የለውም።

በተያያዘ ሌላ ዜና በተለያዩ አካባቢዎች “በመንግስት ኃይሎች ተወሰዱ፤” ያሏቸውን የሰው ሕይወት እስከ ማጥፋት የደረሱ እርምጃዎች በመቃወም በተለያዩ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተካሂደዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት በበኩሉ በአሸባሪነት የሚፈርጃቸውን ሁለት የተቃዋሚ ፓርቲዎች፥ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ’ን) እና ግንቦት ሰባት’ን ተቃውሞዎቹን በመቀስቀስ ይወነጅላል።

በሰላም የሚካሄዱ ሰላማዊ ሰልፎችን፤ ሰላማዊ ጥያቄን ማጠልሸት ለአገሪቷም ሆነ ለመንግስት አይጠቅምም። ሰው ሊገደል ሊደበደብ አይገባም ጥያቄ ስለጠየቀ። የሰለጠነው መንገድ አቅርቦ ማወያየት ነው።

በርዕሱ ላይ የተጠናከሩትን ዘገባዎች ከዚህ ያድምጡ፤

XS
SM
MD
LG