በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

“ተማሪን ተማሪ ገደለው ሲባል ሰምቼ አላውቅም …” - የሟች ሣሙዔል ከተማ አባት


ሟች ሣሙዔል ከተማ(ከማኅበራዊ ሚድያ የተገነ ፎቶ)
ሟች ሣሙዔል ከተማ(ከማኅበራዊ ሚድያ የተገነ ፎቶ)

“በማንኛውም ትግል ውስጥ ተማሪን ተማሪ ገደለው ሲባል ሰምቼ አላውቅም” ሲሉ ሰሞኑን በሮቤው መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የተገደለው ተማሪ ሣሙዔል አባት አቶ ከተማ በቀለ ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል ደግሞ የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና “… ገዥው ፓርቲ ለአንዱ እነ እንትና ናቸው እንደዚህ ያደረጉት፣ ለዚህኛው ደግሞ እንደዚያ ነው እነዚያ ናቸው እንደዚህ ያደረጉት እያሉ የግጭት ሁኔታን ለመፍጠር ከፈለገ ያስቸግራል” ብለዋል፡፡

የተገደለው ሣሙዔል ከተማ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርቱን በተወለደባት ድሬዳዋ ከተማ አጠናቅቆ ለዩኒቨርሲቲ ትምህርቱ ሮቤ ከተማ ወደሚገኘው መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ እንደሄደና የመጀመሪያ ዲግሪውን ለመቀበል የወራት ዕድሜ የቀረው እንደነበር ወላጅ አባቱ አቶ ከተማ በቀለ ገልፀዋል፡፡

ልጃቸው እርሣቸው ጋ ደርሶ ከተመለሰ አንድ ወር እንደማይሞላው ወላጅ አባቱ ነግረውናል፡፡

ጽዮን ግርማ ያጠናቀረችውን ዘገባ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡት፡፡

“ተማሪን ተማሪ ገደለው ሲባል ሰምቼ አላውቅም …” - የሟች ሣሙዔል ከተማ አባት
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:00 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG