በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኦባማ አስተዳደር ለአምስት የዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት አባላት የሰጠው መልስ


ፋይል ፎቶ - የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት
ፋይል ፎቶ - የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት

ባለፈዉ ዓመት በኢትዮጵያ አያሌ ጦማሪያን ከእስር መፈታታቸዉን  መሰረታዊ የሆኑ የስብአዊ መብት ይዞታዎችና የመናገር መብትን ያሻሽላል በሚል ግምት አመስግነን ነበር፣ በቅርቡ ግን ኢትዮጵያ ዉስጥ ጋዜጠኞች እንደገና  መታሰራቸዉ በጥልቁ ያሳስበናል።

በኢትዮጵያ በፕሬስ ነጻነት ላይ የሚታየዉ ቁጥጥር እንዲሁም የጸረ-ሽብር ህጉን በመጠቀም መንግስት ጋዜጠኞች፣ የመብት ታጋዮችና ታቃዋሚዎች ላይ የሚያካሄደዉ አፈና ለዩናትድ ስቴትስ አሳሳቢ በመሆን ለኢትዮጵያ መንግስት እንገልጻለን።

ባለፈዉ ዓመት በኢትዮጵያ አያሌ ጦማሪያን ከእስር መፈታታቸዉን መሰረታዊ የሆኑ የስብአዊ መብት ይዞታዎችና የመናገር መብትን ይሻሻላል በሚል ግምት አመስግነን ነበር፣ በቅርቡ ግን ኢትዮጵያ ዉስጥ ጋዜጠኞች እንደገና መታሰራቸዉ በጥልቁ ያሳስበናል።

የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አርማ
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት አርማ

የኢትዮጵያ መንግስት ቀድሞ የወሰደዉን አዎንታዊ እርምጃ በማጠናከር በነጻነት የመናገር ነጻነትን እንዲያከብር ዴሞክራሲያዊ እርምጃዎችን እንዲያስፋፋ እየጠየቅን፣ የመናገር መብትን ማፈን ሰብአዊ መብቶችን ብቻ ሳይሆን የልማትና የኢኮኖሚ እድገትንም እንደሚገታ መጠቆም እንፈልጋለን።

ኢትዮጵያ በልማት ረገድ ለአፍሪቃ አርአያና ድምጽ ናት፥ ሆኖም ግን እነዚህ የተገኙ ሲኬቶች ቀጣይነት እንዲኖራቸዉ፥ የዴሞክራሲያዊ አስተዳደርና የሰብአዊ መብት ክብር መሰረታቸዉ ሊሆን ይገባቸዋል።

የኢትዮጵያ መንግስት ጋዜጠኞችና ሌሎች መሰረታዊ መብታቸዉን ስለተጠቀሙ ብቻ ያሰራቸዉን ሁሉ እንዲፈታ፣ ወደፊትም የጸረ-ሽብር ሕጉን በመጠቀም ተቃዉሞን እንዳያፍን የጋዜጠኞችን፣ የጦማሪያንን መብት እንዲያከብር እንጠይቃለን።

ኢትዮጵያ ሕብረ ብሔራዊት እንደመሆንዋ ጋዜጠኞች ፥ ጦማሪያን፣ የፖለቲካ ተቃዋሚዎች በነጻነት የመጻፍና የመናገር መብታቸዉ ሊከብር ይገባል።

XS
SM
MD
LG