በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በኦሮሚያ ክልል የተከሰተው ግጭት እንዳሳሰበው አስታወቀ


የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት በኦሮሚያ ክልል የተከሰተው ግጭት በጥልቅ እንዳሳሰበው አስታወቀ።

የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት የተቃዋሚ ሰልፈኞች ሕይወት እንደጠፋበት የተዘገበው በኦሮሚያ ክልል የተከሰተው ግጭት በጥልቅ እንዳሳሰበው አስታወቀ። ሕይወት መጥፋቱ አሳዝኖናል ያለው መግለጫ፥ ለሞቱት ሰዎች ቤተሰቦች ሃዘናችንን እንገልጻለን ይላል።

የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤቱ ቃል አቀባይ ማርክ ቶነር ባወጡት መግለጫ፥ የኢትዮጵያ መንግሥት ለሰላማዊ የተቃውሞ ሰልፎች ፈቃድ እንዲሰጥና አግባብ ያላቸው ቅሬታዎችን ለማስተናገድ ገንቢ ውይይት በማድረግ እንዲያስተናግድ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ያሳስባል ብለዋል።

ሕይወት መጥፋቱ አሳዝኖናል ፥ ለሞቱት ሰዎች ቤተሰቦች ሃዘናችንን እንገልጻለን።
የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት መግለጫ

​ተቃዋሚዎችም ከሁከት ተግባር እንዲቆጠቡና ለውይይት ዝግጁ እንዲሆኑ የዩናይትድ ስቴትስ መንግሥት እንደሚያሳስብ መግለጫው አመልክቷል።

የኢትዮጵያ መንግሥት ጭቅጭቅ ያስነሱ የልማት እቅዶችን ሕዝብ ሳያማክር ተግባራዊ እንደማያደርግ በይፋ ማሳወቁን አስታውሶ መንግሥቱ ምክክሮችን ለማካሄድ የገባውን ይህን ቃል እንደግፋለን ያለው የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መግለጫ፥ የሚመለከታቸውን ወገኖች ያሳተፈ ውይይት ባስቸኳይ እንዲከፍት እናሳስባለን ብሏል።

XS
SM
MD
LG