በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያዊያኑ ደጋፊና ተቃዋሚ ሠልፈኞች ብዛታቸው እንዲስተካከል ቪኦኤን ጠየቁ


please wait

No media source currently available

0:00 0:11:33 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ትናንት፣ መስከረም 27/2007 ዓ.ም በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ፊት ለፊት ሰልፍ ወጥተው የነበሩ የኢትዮጵያ መንግሥት ደጋፊና ተቃዋሚዎች በቪኦኤ በተላለፈው ዜና ላይ የተጠቀሱት ቁጥሮች ትክክል አይደሉም ሲሉ ሁለቱም ቅሬታቸውን አሰምተዋል፡፡

ከመንግሥቱ ደጋፊ ቡድን አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ሙሉ አሰፋ ቁጥራቸው ከአራት መቶ በላይ ይሆን እንደነበረ ገልፀዋል፡፡ ለተቃውሞ የወጡት ሰልፈኞች ቁጥር ከ200 እስከ 250 ይሆናሉ የሚል ግምት እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

ለሰልፍ የወጡትም ባለፈው ሣምንት በኢትዮጵያ ኤምባሲ ቅጥር ግቢ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረው ሁኔታ ውስጥ ተሣትፈዋል የተባሉ ሰዎች በሕግ እንዲጠየቁ ለመጠየቅና ቅሬታቸውንም ለአሜሪካ መንግሥት ለመግለፅ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ከተቃዋሚዎቹ ሰልፍ አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ ግርማ ታፈሰ ደግሞ የእነርሱ ተሰላፊዎች ቁጥር ከ200 እስከ 250 እንደሚሆኑ ገልፀዋል፡፡ የደጋፊዎቹን ቁጥር መገመት ይችሉ እንደሆነ ተጠይቀው “ከመቶ በታች ነው” ብለዋል፡፡

ሰልፉን ያዘጋጁትም ባለፈው የኢትዮጵያ ኤምባሲ አጋጣሚ ወቅት ጥይት የተኮሱት የፀጥታ አታሼ “ከአሜሪካ እንዲወጡ በመደረጋቸው ለአሜሪካ መንግሥት ምሥጋና ለማቅረብ ነው” ብለዋል፡፡

ሁለቱም አስተባባሪዎች ከቪኦኤ ጋር ያደረጉትን ቃለምልልስ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG