በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የኢትዮጵያውያን አትሌቶች ድል በአሜሪካ


ማርቆስ ገነቲ
ማርቆስ ገነቲ

በትላንትናው ሃያ ስድስተኛው የሎስ አንጀለስ ማራቶን ሩጫ ውድድር፥ ኢትዮጵያውያን አትሌቶች በሁለቱም ጾታዎች ድል ተቀዳጅተዋል።

በወንዶቹ ማርቆስ ገነቴ በማራቶን ሲሳተፍ ለመጀመሪያ ጊዜ ቢሆንም፥ የገባበት ሁለት ሰዓት ስድስት ደቂቃ ሰላሳ አምስት ሴኰንድ፥ በካሊፎርኒያ ታሪክ የመጀመሪያው፥ በዓለም ሁለተኛው ፈጣን ጊዜ ሆኖ ተመዝግቦለታል። ከሁሉም በላይ ብዙዎችን ያስደነቀው፥ ትላንት በውድድሩ ወቅት ዝናብ ባይጥል ኖሮ፥ የማርቆስ ጊዜ ከዚህም የበለጠ ፈጣን ሆኖ ሊመዘግብ ይችል እንደነበር መታመኑ ነው።

በሴቶቹ አሸናፊዋ ደግሞ ብዙነሽ ደባ ናት። ሁለቱም ከከተማይቱ ከንቲባና ነዋሪዎቿ ግሩም አቀባበል ተደርጐላቸዋል።

የስፔኑ ሰላሳ ዘጠነኛው ዓመታዊ የዓለም አገር አቋራጭ ሩጫ ደግሞ፥ ዘንድሮም ለሁለተኛ ጊዜ በኬንያ ቀዳሚነትና በኢትዮጵያ ተከታይነት ተጠናቋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፥ አትሊት ፍሬሕይወት ዳዶ ትላንት የተካሄደውን ዓመታዊ የሮም ማራቶን ለሦስተኛ ጊዜ በተከታታይ ድንቅ ጊዜ በማስመዝገብ አሸንፋለች።

እነዚህንና ሌሎች የእግር ኳስ ዜናዎችን ይዟል የምሽቱ የስፖርት ፕሮግራም።

ዝርዝሩን ከዚህ ያድምጡ።

XS
SM
MD
LG