በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አሜሪካ ደቡብ ሱዳን ላይ ማዕቀብ ጣለች


ጆን ኬሪ - የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር
ጆን ኬሪ - የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

ዩናይትድ ስቴትስ በደቡብ ሱዳን ውዝግብ ውስጥ ባሉ በሁለቱም ወገኖች ላይ የመጀመርያውን ማዕቀብ ጣለች።


ደቡብ ሱዳን፣ ከተሞቿና ጎረቤቶቿ
ደቡብ ሱዳን፣ ከተሞቿና ጎረቤቶቿ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:32 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

ዩናይትድ ስቴትስ በደቡብ ሱዳን ውዝግብ ውስጥ ባሉ በሁለቱም ወገኖች ላይ የመጀመርያውን ማዕቀብ ጣለች።

ካለፈው ታኅሣሥ ወር ወዲህ ብቻ በመንግሥቱ ደጋፊዎችና ተቃዋሚዎች መካከል በተካሄደው በዚህ ግጭት በሺህዎቸ የሚቆጠር ሕይወት ጠፍቷል።
ከጎሣ ግጭት ጋር በተያያዘ ጦርነትም ከ1.2 ሚሊየን በላይ ሰው ከቤት ንብረቱ ተፈናቅሏል።

የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ናቸው ማዕቀቡን ትናንት ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 28/2006 ዓ.ም ከአውሮፓ ኅብረቷ የውጭ ፖሊሲ ኃላፊ ካትሪን አሽተን ጋር በተገናኙበት ወቅት ይፋ ያደረጉት።

«ሁለቱም ወገኖች ለጠፋው የሰው ሕይወት ተጠያቂዎች ናቸው» ያሉት ኬሪ፣ አመፁ ከሰው ህሊና በላይ መሆኑንም አልሸሸጉም።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኬሪ መንግሥትም ሆነ የተቃዋሚው ወገን በጠብ ላለመፈላለግ ባለፈው ጥር ወር ያሳለፉትን ስምምነት እንዳላከበሩ አመልክተው አሁን ደግሞ በቅርቡ “የደቡብ ሱዳን መንግሥትም ሆነ ተቃዋሚው ቡድን የወሰዱት እርምጃ ተቀባይነት የሌለው ነው” ብለዋል፡፡

“ደቡብ ሱዳን ተመልሳ ወደ ጦርነትና ውዝግብ ውስጥ እንዳትገባ ዩናይትድ ስቴትስ የተቻላትን ሁሉ ታደርጋለች” ብለዋል ኬሪ።
ሜጀር ጄነራል ማሪየል ቻኑኦንግ
ሜጀር ጄነራል ማሪየል ቻኑኦንግ
የፕሬዚዳንቱ ዘብ ጦር አዛዥ ሜጀር ጄነራል ማሪየል ቻኑኦንግ እና የአማፂያኑ ጦር መሪ ሜጀር ጄነራል ፒተር ጋዴት ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ባሏቸው ንብረቶች ላይም ማዕቀብ እንደሚጣል ነው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኬሪ የተናገሩት።
ጦር መሪ ሜጀር ጄነራል ፒተር ጋዴት
ጦር መሪ ሜጀር ጄነራል ፒተር ጋዴት

የአውሮፓ ሕብረትም ደቡብ ሱዳን ላይ ማዕቀብ ለመጣል ማቀዱን የሕብረቱ የውጭ ጉዳይ ኃላፊ ካትሪን አሽተን ተናግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆን ኬሪ ባለፈው ሣምንት አዲስ አበባ ላይ ከፕሬዚደንት ሳልቫ ኪር ጋር በተገናኘት ወቅት ሚስተር ኪር ከተቀናቃኛቸው ሪያክ ማሻር ጋር የሰላም ስምምነት እንደሚፈራረሙ ነግረዋቸው እንደነበር አይዘነጋም።

ለተጨማሪ ዝርዝር የተያያዘውን የእስክንድር ፍሬውን ዘገባ ያዳምጡ፡፡
XS
SM
MD
LG