በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ሱዳን የምስራቅ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ትብብር ማኅበረሰብ አባል ትሆናለች


የምስራቅ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ትብብር ማኅበረሰብ አባል ፕረዚደንቶች
የምስራቅ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ትብብር ማኅበረሰብ አባል ፕረዚደንቶች

የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባርናባ ሜሪያል ቤንጀሚን ግን ሀገራቸው ከማኅበረሰቡ አባልነት እንደምትጠቀም አስረድተዋል።

ደቡብ ሱዳን በያዝነው ሳምንት (EAC) በሚል አኅጽሮት የሚታወቀው የምስራቅ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ትብብር ማኅበረሰብ አባል ትሆናለች።

የማኅበረሰቡ አባል ሀገሮች መሪዎች ታንዛንያ በተሰበሰቡበት ወቅት ደቡብ ሱዳን ማመልከቻ አቅርባ ተቀብለዋታል። ደቡብ ሱዳን ከኬንያ፣ ከኡጋንዳ፣ ከታንዛንያ፣ ከርዋንዳና ከቡሩንዲ ጋር በመቀላቀል ስደስተኛዋ የምስራቅ አፍሪቃ ማኅበረሰብ አባል መሆኗ ነው።

ፋይል - ፕረዚደንት ሳልቫ ኪር የሰላም ስምምነት ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት የተነሳ ፎቶ
ፋይል - ፕረዚደንት ሳልቫ ኪር የሰላም ስምምነት ንግግር በሚያደርጉበት ወቅት የተነሳ ፎቶ

አንዳንድ ደቡብ ሱዳናውያን በሀገሪቱ ያለውን አለመረጋጋት መሰረት በማድረግ የምስራቅ አፍሪቃ ማኅበረሰብ አባልነትዋ ላይ የመቆጠብ ስሜት አንጸባርቀዋል።

የደቡብ ሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባርናባ ሜሪያል ቤንጀሚን ግን ሀገራቸው ከማኅበረሰቡ አባልነት እንደምትጠቀም አስረድተዋል። ደቡብ ሱዳን የምስራቅ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ማኅበረሰብ አባል የማትሆንበት ምክንያት የለም ሲሉ ከአሩሻ ታንዛንያ ለአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ ተናግረዋል።

“እኛ የተባበሩት መንግስሥታት ድርጅት አባል ነን፣ የምስራቅ አፍሪቃ የልማት ትብብር በይነ-መንግሥታት፣ የሰሜን ኮሪዶርና የግሬት ሌክስ ክልል አባል ነን። ስለሆነም የምስራቅ አፍሪቃ የኢኮኖሚ ማኅበረስብ አባል የምንሆንበት ምክንያት ምንድነው? ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጠይቀዋል።

የማኅበረሰቡ አባል ሀገሮች የመልካም አስተዳደር፣ የዲሞክራሲና በሕገ የመገዛት መርሆችን እንዲከተሉ እንዲሁም ሰብአዊ መብትንና የማበረሰባዊ ፍትህን እንዲያከብሩ ይጠበቅባቸዋል።

XS
SM
MD
LG