በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ሱዳን አውሮፕላን ተከስክሳ 32 የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል


ከጁባ ተነስታ ወደ 800 ሜትር የሚሆን ርቀት ከበረረች በኋላ የደቡብ ሱዳን አውሮፕላን በመከስከሷ 32 የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል። አውሮፕላኗ ሩስያ ስሪት አንተኖቭ መሆኝኗንም ታውቋል።

ከደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ ተነስቶ ወደ ፖላሽ የተባለ በአፐር ናይል (Upper Nile) ወደሚገኝ የነዳጅ ስፍራ ምግብና ሰዎችን ጭና ሲትጓዝ የነበረች አንተኖቭ ወደ 800 ሜትር የሚሆን ርቀት ከተጓዘች በኋላ በናይል ደን ውስጥ መከስከሷ ታውቋል።

በደቡብ ሱዳን አውሮፕላን ተከስክሳ 32 የሚሆኑ ሰዎች ሞተዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:05 0:00

ወደ 32 የሚሆኑ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ አንድ ታዳጊ በህይወት እንደተረፈም ተገልጿል። አውሮፕላኗ ጭናቸው የነበረ 18 ተሳፋሪዎችና ስድስት የአውሮፕላኗ ሰራተኞች ሲሆን ሌሎቹ ሟቾች ተሳፋሪ ስለመሆናቸው እየተጣራ እንደሆነ ሮይተር ዘግቧል።

XS
SM
MD
LG