በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ሱዳን መንግሥትና ተቃዋሚዎች ጁባ ላይ በሚሰፍረው የፖሊስ ኃይል ቁጥር ተስማሙ


የደቡብ ሱዳን ፖሊስ
የደቡብ ሱዳን ፖሊስ

የደቡብ ሱዳን መንግሥትና ተቃዋሚዎች ጁባ ላይ በሚሰፍረው የፖሊስ ኃይል ቁጥር ለረጅም ግዜ ሲወያዩበት በመክረም ዛሬ በሚኒስትሮች የተፈረመውን ሰነድ አጽድቀዋል።

አዲሳባ ላይ እየተወያዩ የሚገኙት የደቡብ ሱዳን መንግሥትና ተቃዋሚዎች፣ ዋና ከተማዋ ጁባ ላይ በሚሰፍረው የፖሊስ ኃይል ቁጥር ተስማምተዋል። በዚሁ መሠረት ተቃዋሚዎቹ ባለፈው መስከረም በመንግሥትና እራሳቸውን «የቀድሞ ታሳሪዎች» ብለው በሚጠሩት ሚኒስትሮች የተፈረመውን ሰነድ ዛሬ አጽድቀዋል።

የተለያዩ ተቋማትን ለመጠበቅ በሚሰማሩት ፭ ሺህ ወታደሮች ስብጥር ላይ ግን ገና ተጨማሪ ውይይት እንደሚያደርጉ ነው የተስማሙት።

እስክንድር ፍሬው ዝርዝሩን ዘግቧል። ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ።

ደቡብ ሱዳን መንግሥትና ተቃዋሚዎች ጁባ ላይ በሚሰፍረው የፖሊስ ኃይል ቁጥር ተስማሙ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:51 0:00

XS
SM
MD
LG