በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ ኮሪያ ወደ ሰሜን ኮሪያ የምታስተላልፈውን የፕሮፖጋንዳ ሥርጭት እንደምትቀጥል አስታወቀች


የደቡብ ኮሪያ ወታደር
የደቡብ ኮሪያ ወታደር

ደቡብ ኮሪያ በነገው እለት በድምፅ ማጉያ መሣሪያ ወደ ሰሜን ኮሪያ የምታስተላልፈውን የፕሮፖጋንዳ ሥርጭት እንደምትቀጥል አስታወቀች።

ፕዮንግያንግ (Pyongyang) በዚህ ሣምንት መግቢያ ላይ ያካሄደችውን የኑሌኬር ጦር መሣሪያ ሙከራ በመቃወም፥ ደቡብ ኮሪያ በነገው እለት በድምፅ ማጉያ መሣሪያ የምታስተላልፈውን የፕሮፖጋንዳ ሥርጭት እንደምትቀጥል አስታወቀች።

ሥርጭቱ ባካባቢው ሰዓት አቆጣጠር ነገ እኩለ ቀን ላይ እንደሚደምር አንድ የፕሬዘዳንቱ ቃል አቀባይ ገልጿል።

ሁለቱ ሀገሮች እ አ አ ከ 1950 - 1953 ዓም ጦርነት ማካሄዳቸው ሲታወስ፥ እስካሁን ድረስ አልፎ አልፎ ይቆራቆሳሉ። ባለፈው ዓመት ነሐሴ ለምሳሌ በሥርጭቱ ሳቢያ የከባድ መሣሪያ ተኩስ ተለዋውጠዋል። ደቡብ ኮሪያ መተነኳኮሱን ለማስወገድ ያስችላል የተባለ ስምምነት ከፕዮንግያንግ (Pyongyang)ጋር ከደረሰች በሁዋላ፥ ፕሮፓጋንዳ ማሠራጨቷን አቁማ ነበር።

ሰሜን ኮሪያ ትላንት የሐይዶጅን ቦምብ መሞከሯ፥ የተደረሰውን ስምምነት ይጥሳል ሲሉ፥ የፕሬዘዳንቱ ከፍተኛ የብሄራዊ ፀጥታ አማካሪ በመግለጫቸው አስታውቀዋል።

የአቶሚክ እና የሃይድሮጅን ቦምብ ልዩነቱ ምንድን ነው?
please wait

No media source currently available

0:00 0:00:54 0:00

ሠራዊታችን በሙሉ ተጠንቀቅ ላይ ይገኛል፥ ሰሜን ኮሪያ ልተናኮስ ካለች ከባድ ቅጣት ይደርስባታል ሲሉም አስጠንቅቀዋል።

የዜና ዘገባ አለን የድምጽ ፋይሉን በመጫን ያዳምጡ።

ደቡብ ኮሪያ ወደ ሰሜን ኮሪያ የምታስተላልፈውን የፕሮፖጋንዳ ሥርጭት እንደምትቀጥል አስታወቀች
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:18 0:00

XS
SM
MD
LG