በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኤች አይ ቪን ለመከላከል የተሰራጨው መድሃኒት አጥጋቢ ውጤትን አስመዘገበ ተባለ


ፋይል ፎቶ
ፋይል ፎቶ

ኤች አይ ቪ ኤድስን ለመከላከል የሚረዳ መድሃኒት ለማግኘት አበረታች ሳይንሳዊ ጥናቶች መኖራቸው፤ የፈውስ መድሃኒትን ለማግኘት የተያዙ ምርምሮችና፤ የቫይረሱን መቋቋሚያ እንክብሎች ቫይረሱን ለመከላከል ማስቻላቸው፤ በዚህ ሳምንት በደቡብ አፍሪካ ደርባን እየተካሄደ በሚገኘው አለም አቀፉ የኤድስ ጉባዔ አትኩሮት የተደረገባቸው ጉዳዮች ሆነዋል።

የህክምና ባለሙያዎቹ ቫይርሱን ለማጥፋት የሚረዳ መድሃኒት መቼ እንደሚገኝ ባይታወቅም በመድሃኒቱ ላይ የሚደረገው ጥናት ግን አበረታች ግኝቶች የታየበት ነው ብለዋል።

በተለይም ቫይረሱን ለመከላከል የሚረዳው አንቲሪትሮቪራል /antiretroviral/ በመባል የሚታወቀው እንክብል በቀን አንዴ ከተወሰደ ቫይረሱን የመከላከል ብቃቱ ተረጋግጦለታል።

በደርባን እየተካሄድ በሚገኘው 21ኛው አመታው የኤድስ ጉባዔ ላይ የህክምና መድሃኒት አጥኚዎቹ ይህ እንክብል አጥጋቢ ውጤት እንዳመጣ ተናግረዋል።

ለኤች አይ ቪ ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ ለተጋለጡት ሰዎችን በተመለከተ የደርባኑ ጉባዔ አፅኖ ሰጥቶ ተነጋግሮበታል። እንደ ጥናቱ ገለፃ ቫይረሱ በደማቸው የተገኘባቸው ሰዎች የሚወስዱትን መድሃኒት ለቫይረሱ የተጋለጡ ሰዎች የመከላከያ እንክብሉን አንቲሪትሮቪራል /antiretroviral/ በቀን አንዴ በመውሰዳቸው የቫይረሱን ስርጭት በጣም እንዲቀንስ ሆኗል።

ሄትሮ ድሩግ ሊሚትድ የተባለው የህንድ የመድሃኒት አምራች ኩባንያ እንዚህን እንክብሎች በማምረት ላይ ይገኛል። የኩባንያው የሽያጭ ክፍል ሃላፊ ራሁል ላንዴ መድሃኒቱ እንዴት እንደሚሰራ ይናገራሉ።

እስከአሁን በተደረገው ጥናት ኤች ቪ ቲ ኤን 702 የተባለውም የመከላከያ መድሃኒት በታይላንድ ተገኝቶ ስኬታማ ሆኗል። በዚህ አመት በደቡብ አፍሪካና በሌሎች የአፍሪካ ሃገሮች በዚህ አመት መገባደጃ ላይ ይሰራጫል ተብሎ ይጠበቃል። ዶ/ር ፏውሲ እንዳሉት የመድሃኒቱን ውጢታማነት ለማየት ምናልባትም ጊዜን ሊወስድ ይችላል።

የኤች አይ ቪ ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት ከግብረስጋ ግንኙነት መታቀብ የሚለው አካሄድ ውጤት እንደማያመጣ፤ በስራው የተሰማሩ እየተናገሩ ነው።

ቫይረሱ በደማቸው የተገኘባቸውን ሰዎች በመንከባከብ ዙሪያ የሚሰሩት ጁሊያን የግብረስጋ ግንኙነቶች ጥንቃቄ የተሞላበት እንዲሆን በግልፅ ማስተማር ይገባናል ብለዋል።

በግልጽ ውይይት ላይ የተመሰረተ መማማር እንደሚያስፈልግና በተለይም አዳጊ ወጣቶች ላይ ግንዛቤ በማስጨበጥ ዙሪያ የበለጠ መሰራት እንደሚገባው የአለም አቀፉ ኤድስ ጉባዔ ጥኩረት ሰጥቶ ተነጋግሮበታል። ይህ አመታዊ አለም አቀፍ የኤድስ ጉባዔ በነገው እለት ይጠናቀቃል።

አኒታ ፖል እና ቱሶ ኩማሎ ያጠናቀሯቸውን ዘገባዎች መስታዎት አራጋው አዘጋጅታለች። ከበታች ያለውን ድምፅ በመጫን ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ።

ኤች አይ ቪን ለመከላከል የተሰራጨው መድሃኒት አጥጋቢ ውጤትን አስመዘገበ ተባለ
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:08 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG