በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

አል-ሻባቦች ሁለት መሪዎቻቸውን ገደሉ


ሶማሊያ
ሶማሊያ

የአል-ሻባብ ተዋጊዎች ሁለት መሪዎቻቸውን ዛሬ መግደላቸውን የአማፂው ቡድን ቃል አቀባይ ዛሬ አስታወቀ፡፡ አንደኛው የአምስት ሚሊየን ዶላር ጉርሻ የታወጀበት ነው፡፡





ሶማሊያ
ሶማሊያ

please wait

No media source currently available

0:00 0:03:51 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

የአል-ሻባብ ተዋጊዎች ሁለት መሪዎቻቸውን ዛሬ መግደላቸውን የአማፂው ቡድን ቃል አቀባይ ዛሬ አስታወቀ፡፡ አንደኛው የአምስት ሚሊየን ዶላር ጉርሻ የታወጀበት ነው፡፡

አብዱልአዚዝ አቡ ሙስ’አብ ባሠራጨው የድምፅ መልዕክት የሙጃሕዲኑ ታጣቂዎች በመካከላቸው መከፋፈልን ለመፍጠር ይጥሩ በነበሩ በአባሎቻቸው ላይ ዘመቻ ካካሄዱ በኋላ የተወሰኑትን በቁጥጥር ሥር ማዋላቸውንና አንዳንዶቹ ደግሞ እጅ ለመስጠት አሻፈረኝ ማለታቸውን አመልክቷል፡፡

“ሁለቱ እጃቸውን እንዲሰጡ ሲጠየቁ አሻፈረን ብለው አንገራገሩ፣ በተኩስ መካከል ተገደሉ፤ አምላክ ነፍሳቸውን ይማርና በገነት ያስቀምጥ፡፡ ሃሣቡ እነርሱን ለመግደል አልነበረም፡፡ በቁጥጥር ሥር አውለን እሥልምና ችሎት ፊት ልናቀርባቸው ነበር፡፡” ነው የሚለው ከዚህ ጋር የተያያዘው አብዱልአዚዝ በሶማሊኛ ያሠራጨው መልዕክት፡፡

ሰዎቹ የተገደሉት ከሞቃዲሾ 350 ኪ.ሜ በስተደቡብ በምትገኝ ብራቫ የምትባል ከተማ ውስጥ እንደሆነ ታውቋል፡፡

የተገደሉት ሰዎች እነማን እንደሆኑ የአል-ሻባብ ቃል አቀባይ አልተናገረም፡፡ ይሁን እንጁ የቪኦኤ ሶማሊኛ አገልግሎት የተለያዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን አነጋግሮ ኢብራሂም ሃጂ ጃማ ወይም ኢብራሂም አል-አፍጋን ወይም በተቀጥያ መጠሪያው አቡ ባካር አል-ዛይሊዪ እየተባለ ይጠራ የነበረውና ሼኽ አብዲሃሚድ ሃሺ ኦልሃዬ ወይም በቅፅል ሞዐሊም ቡርሃን መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡

መሪዎቹ የተገደሉት የዛሬ አሥር ቀን ሰኔ 12 መሆኑንም የቪኦኤ ምንጮችን የጠቀሰው የሶማሊኛ አገልግሎት ዘገባ አመልክቷል፡፡

የአል-ሻባብ ምንጮች እንደሚሉት አል-አፍጋን የተገደለው ከመስጂስ እየወጣ ሳለ በተተኮሰበት ተርታ ጥይት ሲሆን ሙዐሊም ቡርሃን የተገደለው ከቤቱ ተይዞ ከተወሰደ በኋላ ነው፡፡

ሌሎችም ተኩሶች የተሰሙ እንደነበረ ቢታወቅም የደረሰ ጉዳት ወይም ጥፋት ይኑር አይኑር ለጊዜው አልታወቀም፡፡

ይህ አጋጣሚ ከተፈጠረ ከሁለት ቀናት በኋላ ለተገደሉት ሁለት ሰዎች የቅርብ ወዳጅ እንደነበረ የሚነገረው ዋነኛው የአል-ሻባብ መሪ ሼኽ ሐሰን ዳሂር አዌይስ ከአካባቢው በጀልባ ካመለጠ በኋላ ማዕከላዊ ሶማሊያ ውስጥ ተይዞ እጁ ለመንግሥት መሰጠቱ ይታወቃል፡፡

ከተገደሉት አንዱ ኢብራሂም አል-አፍጋን በአል-ሻባብ ውስጥ በርካታ የሥልጣን ቦታዎች የነበሩት ሲሆን የቡድኑ ምክትል መሪ፣ የገንዘብ መምሪያው ኃላፊና የኪስማዮ ገዥ ሆኖ ሠርቷል፡፡

ተይዘው ለፍርድ እንዲቀርቡ ያሉበትን መረጃ ለሚሰጥ በእያንዳንዳቸው ራስ የአምስት ሚሊየን ዶላር ጉርሻ እንደምትሰጥ ዩናይትድ ስቴትስ ማስታወቂያ ካወጣችባቸው ሰባት የአል-ሻባብ መሪዎች አል-አፍጋን አንዱ ነው፡፡

አል-አፍጋን ዩናይትድ ስቴትስ፣ ቨርጂንያ ውስጥ ይኖር የነበረ ሲሆን እአአ በ1980ዎቹ ውስጥ ከሙጃሕዲን ጎን ተሰልፎ ለመዋጋት ወደ አፍጋኒስታን መሄዱንና በ1991 ዓ.ም የሶማሊያ ማዕከላዊ መንግሥት ሲወድቅና ሥርዓተ-መንግሥቱ ሲፈራርስ እጅግ የከፋ ዓይነት ጂሃድ ወደ ሶማሊያ ማስገባቱና ሶማሊያ ውስጥ የመጀመሪያውን የጂሃድ ማሠልጠኛ ሠፈር ማቋቋሙን ዘገባዎች ይጠቁማሉ፡፡

አል-አፍጋን ከአል-ቃይዳው መሥራችና መሪ ኦሣማ ቢን ላደን ጋርም ብዙ ግንኙነቶች እና ንግግሮች እንደነበሩት ቢን ላደን በ2011 ዓ.ም ከተገደለ በኋላ ሲናገር ይሰማ እንደነበር ታውቋል፡፡

ሌላው ተገዳይ ሙአሊም ቡርሃን አል-ሻባብ ውስጥ ዋነኛ የሚባል የሃይማኖት ሊቅ እና የቡድኑ የመማክርት ምክር ቤት አባል እንደነበረ ተገልጿል፡፡

ሶማሊያ
ሶማሊያ
XS
SM
MD
LG