በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማልያ በለድወይኔ ከተማ አሮፕላን ጣቢያ መግቢያ ላይ የደረሰ ጥቃት ስድስት ሰዎች ቆስለዋል


ማዕከላዊቷ የሶማልያ በለድወይኔ ከተማ
ማዕከላዊቷ የሶማልያ በለድወይኔ ከተማ

በበለድወይኔ ከተማ አሮፕላን ጣቢያ መግቢያ ላይ የደረሰ ጥቃት፣ ሁለት የአፍሪቃ ሕብረት ወታደሮችን ጨምሮ ቢያንስ ስድስት ሰዎች መቁሰላቸው ከፖሊስ የተገኘ መረጃ አመለከተ።

በማዕከላዊቷ የሶማልያ በለድወይኔ ከተማ አሮፕላን ጣቢያ መግቢያ ላይ የደረሰ ጥቃት፣ ሁለት የአፍሪቃ ሕብረት ወታደሮችን ጨምሮ ቢያንስ ስድስት ሰዎች መቁሰላቸውን፣ የሞተ ግን እንደሌለ፣ ዛሬ ሰኞ ከፖሊስ የተገኘ መረጃ አመለከተ።

የበለድወይኔ ከተማ ፖሊስ ኰሚሽነር ኰሮኔል አሊ ዳሁ አብዲ ለአሜሪካ ድምጽ በሰጡት ቃለ-ምልልስ፣ "የደኅንነት ጥበቃ ጓዶች ወደ አየር ማረፊያው የሚያመሩ ተሸከርካሪዎችን በሚፈትሹበት ወቅት፣ ከላብቶፕ (laptop) ኮምፒተር ጋር የተያያዘ ቦምብ ፈንድቶ ነው፣ አራቱን ሶማሌዎችና ሁለቱን የጂቡቲ ዜግነት ያላቸውን የአፍሪቃ ሕብረት ወታደሮች ያቆሰለው" ብለዋል።

ከፍንዳታው በኋላ የመንገደኞችን ደህንነት ለማረጋገጥ በተካሄደ ፍተሻ በሕይወት ላይ የደረሰ ጉዳት እንደሌለ መረጋገጡንና እንደ ዕድል ሆኖም አንድ ያልፈነዳ ቦምብ ከሌላ ኮምፒተር ጋር መገኘቱን ኮረኔል አብዲ ለአሜሪካ ድምጽ ጨምረው ገልጸዋል።

ከዛሬው ፍንዳታ ጋር በተያያዘ በተካሄደው ዘመቻ፣ አንዳንድ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውንም ኮረኔሉ አልሸሸጉም። አጭር የዜና ዘገባውን ለማዳመጥ የድምጽ ፋይሉን ይጫኑ።

በሶማልያ በለድወይኔ ከተማ አሮፕላን ጣቢያ መግቢያ ላይ የደረሰ ጥቃት ስድስት ሰዎች ቆስለዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:01:11 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG