በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከሶማሊያ ድንበር ተሻግረው ከ17 ሺህ በላይ ስደተኞች ወደኢትዮጵያ ጎዴ አካባቢ ገቡ፡፡


ከሶማሊያ ድንበር ተሻግረው ከ17 ሺህ በላይ ስደተኞች ወደኢትዮጵያ ጎዴ አካባቢ ገቡ፡፡

በዶሎ ኦዶ ኮቤ የስደተኞች መጠለያ ረሃብ እየገደለው ያለው ሰው ቁጥር አሁንም ከፍተኛ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አስታውቋል፡፡

ስደተኞቹ የኢትዮጵያን ድንበር እያቋረጡ መግባት የጀመሩት ከስድስት ሣምንታት ወዲህ መሆኑን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽነርና የኢትዮጵያ መንግሥት ቃኚዎች ጥምር ቡድን አረጋግጧል፡፡

የመግቢያ በሮቹ በጎዴና በአፍዴር አካባቢዎች የሚገኙ ሲሆኑ ቡድኑ ቀደም ሲል ተንቀሣቅሶ የነበረው የ2 ሺህ ስደተኞችን ሁኔታ ለመመልከት እንደነበረ ተዘግቧል፡፡

ከእነዚህ 17 ሺህ 500 ስደተኞች ከዘጠና ከመቶ በላይ የሚሆኑት ሕፃናትና ሴቶች ሲሆኑ በምግብና በውኃ እጦት እንዲሁም በበሽታ እየተሰቃዩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ለዝርዝሩ ዘገባውን ያዳምጡ፡፡

XS
SM
MD
LG