በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለኦጎኒላንድ የአካባቢ ብክለት የሼል ኩባንያና የናይጄሪያ መንግስት ተጠያቂ ናቸዉ


ዓለም አቀፉ የስብአዊ መብት ተሙዋጋች ድርጅት አምነስቲ ኢንተርናሽናልና (Amnesty International) ሌሎች የመብት ድርጅቶች የሼል ኩባንያ በኒጄር ዴልታ በአራት አካባቢዎች ያፈሰሰዉን ነዳጅ አጽድቼአለሁ ማለቱ ከእዉነት የራቀ ነዉ አሉ።

በናይጄሪያ የኒጄር ዴልታ ኦጎኒላንድ የነበረዉ የአካባቢዉ ብክለት እጅግ ከፍተኛ ስለነበረ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የከባቢ ደህንነት ፕሮግራም እንደ አዉሮፓ አቆጣጠር በ 2011 ባወጣዉ ጥናት ለማጽዳት ብዙ አስርተ ዓመታትን ይወስዳል ብሎ ነበር።

የሰብአዊ መብት ተንከባካቢዉ ድርጅት አምነስቲ እንተርናሽናል በበኩሉ፥ የሼል ኩባንያ ከዓመታት በፊት አጸዳሁዋቸዉ ባላቸዉ ነዳጅ በፈሰሰባቸዉ አካባቢዎች ”በዓይን የሚታይ” ያለዉ የአካባቢ ብክለት መኖሩን ይናገራል።

የአሜሪካ ድምጽ ዘጋቢ ክሪስ ስተይን(Chris Stein) ከአክራ ዘገባ ልኮአል፣ ትዝታ በላቸዉ ታቀርባለች።

ለኦጎኒላንድ የአካባቢ ብክለት የሼል ኩባንያና የናይጄሪያ መንግስት ተጠያቂ ናቸዉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:17 0:00

XS
SM
MD
LG