በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በቦልቲሞር ከተማ በሚገኝ መስጊድ ያደረጉት ንግግር


ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በቦልቲሞር ከተማ በሚገኝ መስጊድ ያደረጉት ንግግር
please wait

No media source currently available

0:00 0:02:38 0:00

ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በቦልቲሞር ከተማ በሚገኝ መስጊድ ያደረጉት ንግግር

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በቦልቲሞር ከተማ በሚገኝ መስጊድ ተገኝተው፣ የቦልትሞር የሙስሊም ማኅበረሰብ በተባለ ተቋም የእስልምና እምነት ተከታይ ከሆኑ አሜሪካውያን ጋር ተገናኝተው ተነጋግረዋል።

የዩናይትድ ስቴትሱ ፕሬዝዳንት ባራክ ኦባማ በአስተዳደር ዘመናቸው የመጀመሪያው የሆነውን በአንድ የዩናይትድ ስቴትስ መስጊድ በሚያደርጉት ጉብኝት የቦልትሞር የሙስሊም ማኅበረሰብ በተባለ ተቋም የእስልምና እምነት ተከታይ ከሆኑ አሜሪካውያን ጋር ተገናኝተው ይነጋገራሉ።
“ይህ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት የእስልምና እምነት ተከታይ የሆናችሁ አሜሪካውያን እንደ ባሕልና ወጋችሁ ፈጣሪያችሁን ለማምለክ በዚህች አገር ያላችሁን መብትና ባሕላችሁን ለማስጠበቅ ያላቸውን ጠንካራ አቋም የሚያንጸባረቅ አጋጣሚ ነው፤” ሲሉ የዋይት ሃውሱ ቃል አቀባይ ጆሽ እርነስት (Josh Ernest) በትላንትናው ዕለት በሰጡት አስተያየት የፕሬዝዳንቱን ጉብኝት ፋይዳ አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል።
ኦባማ በቦልቲሞር ከተማ በሚገኝ መስጊድ ተገኝተው ለዕምነቱ ተከታዮች ከሚያሰሙት ንግግር አስቀድሞ፤ ሥጋታቸውን ለመረዳትና “ሃሳባቸውን ለመስማት” ከሙስሊም አሜሪካውያን መሪዎች ጋር በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት የሚሳተፉ መሆናቸውን የዋይት ሃውስ መግለጫ አመልክቷል።
ኦባማ ከዚህ ቀደም በውጭ አገሮች የሚገኙ የተለያዩ መስጊዶችን ጎብኝተዋል።

XS
SM
MD
LG