በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሮማውን ርዕሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት የዋይት ሀውስ ጉብኝት


ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ፣ የሮማውን ርዕሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት አባ ፍራንሲስን ዛሬ ረቡዕ ማለዳ ላይ በዋይት ሀውስ ተቀብለው አነጋገሩ።

ፕሬዚደንት ባራክ ኦባማ የሮማውን ርዕሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት አባ ፍራንሲስን በዋይት ሀውስ ውስጥ በኦፊሴል ተቀብለው አነጋገሩ። አምላካችን እግዚአብሔር የርዕሰ-ሊቃነ ጳጳሳቱን የፍቅርና የተስፋ መልዕክት በመስጠቱ፣ በአገራችንና በመላው ዓለም ያሉ ሕዝቦችን ማነቃቃቱ እንዴት ድንቅ ቀን ነው፣ በማለት ኃይለ-ቃል አሰምተዋል።

ዋይት ሀውስ እንደገለጸው፣ በአቀባበሉ ወቅት ፕሬዚደንት ኦባማ ስለ አቡኑን ሲናገሩ በዚህ ጉብኝትዎ ዙሪያ የሚገኘው ደስታ የሚመነጨው፣ እንደ ሊቀ-ጳጳስ ካለዎ ሚና ብቻ ሳይሆን እንደ ሰውም ከሚያሳዩት ልዩ ባሕሪ ጭምር ነው ብለዋል።

እነዚህም ትህትናዎ፣ ውስብስብ ያልሆነውና ቀለል ያለ አቀራረብዎ፣ ከአንደበትዎ የሚወጡት እርጋታ የተመላባቸው ቃሎችዎና ለጋስ ቡራኬዎ ናቸው።

ሊቃነ-ጳጳሳት አቡነ ፍራንሲስ በበኩላቸው፣ ዩናይትድ ስቴትስ በዓለማችን ያላትን ሚናና የምታበረክታቸውን አያሌ መልካም ነገሮች አወድሰው፣ በለሆሳስ ባሰሙት ቃል፣ "እግዚአብሄር አሜሪካን ይባርክ"ብለዋል።

ለዝርዝሩ የተያያዘውን የአዲሱ አበበን ዘገባ ያዳምጡ፡፡

የሮማውን ርዕሰ-ሊቃነ-ጳጳሳት የዋይት ሀውስ ጉብኝት 4'49"
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:49 0:00
ቀጥተኛ መገናኛ

XS
SM
MD
LG